በከተማችን የኃይል መቆራረጥ ችግር የሚያጋጥማቸውን ኢንዱስትሪዎች የሶላር ኃይል አቅርቦት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር 667 ኢንዱስትሪዎች ያሉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 149 የሚሆኑት የኃይል መቆራረጥ ችግሮች እንደሚያጋጥማቸው ቢሮው ጠቁሟል፡፡ከእነዚህ ውስጥ ከአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በመነጋገር የ36 አምራች ኢንዱስትሪዎችን ችግሮች መቅረፍ መቻሉን የአዲስ አበባ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታውቋል ፡፡

የኃይል መቆራረጥ ችግሮች እየገጠሟቸው የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች በሙሉ አቅማቸው እንዲያመርቱ ሶላር ኃይል አቅርቦት ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰሩ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ከፍያለው ወልደመስቀል ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡ቢሮው ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር በጉዳዩ ላይ ተወያቷል፡፡

ዘጋቢ ቤዛዊት ግርማ

ቀን 22/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply