በከተማዋ ውስጥ በተለያየ መንገድ ገብተው እየኖሩ ያሉ ስደተኞች እና የመኖርያ ቪዛቸው ያለፈባቸው የውጭ ዜጎችን የመመዝገቡ ሥራ መጀመሩ ተገለፀ

ሐምሌ 12 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በተለያየ መንገድ ገብተው እየኖሩ ያሉ ስደተኞች እና የመኖርያ ቪዛቸው ያለፈባቸው የውጭ ዜጎችን የመመዝገብ ሥራ መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ አስታውቋል።

ኤጀንሲው በኢምግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት አገልግሎት እየተመራ ያለውን የስደተኞች እና የውጭ ዜጎች ምዝገባ ሥራ ትናንት ሐምሌ 11 ጀምሮ በኹሉም ክፍለ ክተሞች ወረዳ ጽ/ቤቶች በይፋ መጀመሩን ነው የገለጸው።

ምዝገባውም በከተማዋ የሚኖሩ ስደተኞችን እና የውጭ አገር ዜጎችን በተገቢው መረጃ መዝግቦ ለመያዝ የሚያስችል መሆኑም ተነግሯል።

በትላንትናው ዕለትም በርካታ ስደተኞች እና የውጭ አገር ዜጎች ወደ ምዝገባ ጣቢዎች እየቀረቡ በመመዝገብ ላይ መሆናቸውን የገለጹት መሆኑን የኤጀንሲው ም/ዋና ዳይሬክተር ዮናስ አለማየሁ ተመዝጋቢዎች ከተመዘገቡ በኋላ የምዝገባ ማረጋገጫ እየወሰዱ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡

ምዝገባው እስከ ሐምሌ 25 ቀን 2014 በተያዘው መርሃ ግብር መሰረት የሚቀጥል ሲሆን፤ በዚህ የምዝገባ ሂደት የማያልፍ ስደተኛ እና የውጭ ዜጋ አለመኖሩን ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልፀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply