በከተማዋ የሚታየውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ ጥብቅ የቁጥጥር ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ባለስልጣን በመዲናይቱ የሚታየውን የትራንስፖርት ዕጥረት ለመቅረፍ ከ5 መቶ በላይ የሚሆኑ ሀገር አቋራጭ አውቶብሶችን ወደ ስራ አስገብቶ ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት እያደረገ መሆኑን  ጠቁሟል፡፡

የባለስልጣኑ የህዝብ ጭነት ትራንስፖርት ስምሪትና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ተስፋሁን አሁን ላይ 460 የሚሆኑ አውቶቢሶች በሁሉም አካባቢዎች ላይ ተሰማርተው አገልግሎቱን በመስጠት ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ዕጥረቱን ለመቅረፉ በታክሲዎች ትራስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች ላይ የቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡አቶ ዮሴፍ አክለውም በትምህርተ ቤቶች ላይ ከ100 በላይ የሚሆኑ የሸገር ብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ አስታወቀዋል፡፡

*****************************************************************************

ዘጋቢ፡ አብርሃም አያሌው

ቀን 19/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply