በከተማ ውስጥ የሚገኙ ህንፃዎች ቆጠራ እየተካሄደ ነው:: በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ህንፃዎች መረጃቸው በአግባቡ ባለመደራጀቱ ምክንያት ቆጠራ እየተካሄደባቸው ነው ተብሏል፡፡ቆጠራው ከተ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/FQaNsJ7a4Qsmp7rSIWazYbm4gPk2jzvBLFmmhkobVJyr62SD03i73IXWC41u-uhMnofLAnCHh2lrGO5-CgulXt_w4B81_eF2jCawTFUoFYwB6iYi-RhhedmL2OwkHQMux-JBJfW5eG7pJGU1n8naIVDWX4hCFhMzvGGXqwwF8y14fVfkTc6FaenK53P-OvQh4ZpJ01ukAiHukuUISbQfng5-dcoDUj2Y47doePxnym0L4ZYm1gBK3eMPUJepI81rN9HsRnaMf-YFLj-9gXZ9JclKUESzpPQbod975M-srmbf7A8ntQsysrUGV7UEZ6Pg9fZIHWsX737b_HDj2QwJgQ.jpg

በከተማ ውስጥ የሚገኙ ህንፃዎች ቆጠራ እየተካሄደ ነው::

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ህንፃዎች መረጃቸው በአግባቡ ባለመደራጀቱ ምክንያት ቆጠራ እየተካሄደባቸው ነው ተብሏል፡፡

ቆጠራው ከተማ ውስጥ ያሉ ህንፃዎችን መረጃ በዘመናዊ መንገድ ለማደራጀት ያለመ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ዳዊት ሁንዴሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ከተማ ውስጥ የሚገኙ በጅምር ያሉትን ህንጻዎች ጨምሮ ግንባታቸው ተጠናቀው አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ህንፃዎች ቆጠራ እንደሚደረግላቸው ገልፀዋል፡፡

ኢንጅነር ዳዊት እንዳሉት፣ የመረጃ አያያዙ በተለያዩ ምክንያቶች ችግር የነበረበት በመሆኑ የህንፃ መረጃዎችን በተገቢው መንገድ በመሰብሰብ መረጃ አያያዙን ማዘመን እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

የህንፃ ቆጠራው በሁለት ወራት ውስጥ በማጠናቀቅ በከተማ አስተዳደሩ በኩል ውጤቱ ይፋ ይደረጋልም ተብሏል፡፡

በህንፃ መረጃ አሰባሰቡ ላይ ግንባታቸው ተጀምረው የቆሙ እንዲሁም ባለቤት አልባ ህንፃዎችን በተመለከተም ከመረጃ አሰባሰቡ በኃላ ውሳኔ እንደሚሰጥባቸው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ
የካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም

ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply