በከፍተኛ መስዋትነት ነጻ በወጣው የራያ አካባቢ ነዋሪዎች ላይ ተጨማሪ የመከራ ጊዜን ለማራዘም በሕወሓት መልዕክተኝነት እየሰሩ ነው የተባሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ…

በከፍተኛ መስዋትነት ነጻ በወጣው የራያ አካባቢ ነዋሪዎች ላይ ተጨማሪ የመከራ ጊዜን ለማራዘም በሕወሓት መልዕክተኝነት እየሰሩ ነው የተባሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ተጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 20 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ራያ ሕወሓት ከበርካታ ዓመታት በፊት በሴራና በጉልበት ከያዛቸው የአማራ አፅመ እርስቶች መካከል አንዱ ነው። ቡድኑም በራያ አማራዎች ላይ የማንነት ጥያቄ አነሳችሁ በሚል አያሌ ጀግኖችን ገድሏል፣ አድራሻቸውን አጥፍቷል፣ አቁስሏል፣በግፍ በእስር ቤት እንዲያረጁና እንዲሞቱ ማድረጉ ይታወቃል። ዛሬ ህዳር 20 ቀን 2013 ዓ.ም በግለሰብም ሆነ በተቋም ደረጃ የሚንቀሳቀሱ አካላትን ለማስተካከል ያለመ የወጣቶች ውይይት በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ እና በመርሳ ስለመደረጉ የገለፀው የአማራ ወጣቶች ማህበር ሊቀመንበር ወጣት አስናቀ መንገሻ ነው። ከሃዲው ሕወሓት በራያ ነዋሪዎች ላይ በቀጥታ ከሚያደርሰው ጥቃት በተጨማሪ ከፍተኛ ገንዘብ በመርጨት በባለጭምብሎች ወይም በተላላኪዎች በኩልም ሲያስፈፅም ቆይቷል ያለው ወጣት አስናቀ እንደማይሳካላቸው ቢታወቅም ዛሬም ሕወሓት ወደ መቃብር እየወረደ ባለበት ሁኔታ እንኳ ተከፋዮች ነጻ የወጣውን ራያን ወደ ዳግማዊ አፈና እና ባርነት ለመመለስ እየተፍጨረጨሩ ነው ብሏል። ወጣት አስናቀ እንደገለፀው የራያ ጢነኛ የአማራ ወጣቶች ማህበርና ስበር ራያ በዛሬው እለት ራያ ቆቦ እና መርሳ ላይ ውይይት አድርጓል። “የራያ ህዝብ በቋንቋው፣በወጉ ፣በባህሉ፣በስነ ልቦና ውቅሩ አማራ ነው፣ በመሆኑም ከሚወደው የወሎ አማራ ህዝብ ጋር አብሮ በሰላም ይኖራል፤ በከፍተኛ መስዋዕትነት ያገኘውን ነጻነትንም ያጣጥማል፤ ከዚህ አፈንግጠው በሕወሓት ተልዕኮ አስፈጻሚነት የሚያደናግሩትን አካላትንም ይታገላል!” የሚለው ዋነኛ የመድረኩ አጀንዳ ነበር ብሏል። በመድረኩ ላይ ከዚህ በፊት ከቡድኑ ገንዘብ በመቀበል በተላላኪነት በማገልገል ንፁሀንን ሲያስገድሉና በሽህዎች የሚቆጠሩትን አሳፍነው ያስወሰዱና አሁንም በሽብር ተግባር የተሰማራን ቡድን አላማ ለማሳካት የሚጥሩ አካላት ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል። ማንነትንና እርስት ጠየቃቹህ በሚል ልጆቹ ተገድለውበት፣ ታስረውበትና የብዙዎች መዳረሻም ጠፍቶት ሀዘን ላይ በተቀመጠ ህዝባችን ላይ የትናንቱን አፈና ለመድገም የሚሯሯጡ ባለጭምብሎች እንዲስተካከሉ ነው ወጣቶቹ ያሳሰቡት። ራያን ለመከፋፈል ሲሉ በከሰረው የሕወሓት መንገድ በመጓዝ አዲስ ማንነት ሳይቀር ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ ግለሰቦችና ተቋማት ከክፉ አካሄዳቸው ቶሎ እስካልተመለሱ ድረስ ግን በሕግ ተጠያቂ ይደረጋሉ፤ ስለህዝብ ሲባል ከነዋሪዎች ጋር በመተባበር እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደዱ ነው ወጣት አስናቀ የገለፀው። በላስታላሊበላ፣በቡግና፣በዋልድ፣በወልዲያና በሁሉም ወረዳዎች ህዝባዊ ውይይቶች እንደሚቀጥሉ ተገልጧል። በተመሳሳይ እለት በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ሆቴልም እነ ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ፣ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ አቶ ዛዲግ አብርሀና ሌሎችም በተገኙበት በመስዋዕትነት ከሕወሓት ጭቆና ነጻ በወጣው ራያ ጉዳይ ሰፊ ምክክር ስለመደረጉ ነው ወጣት አስናቀ የጠቆመው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply