በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚሰማሩ የፖሊስ አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚሰማሩ የፖሊስ አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17 ቀን 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚሰማሩ የፖሊስ አባላት ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።
ስልጠናው በሰንዳፋ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ሚኒስቴሩ ከፌዴራል ፖሊስ እና ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ነው እየሰጠ የሚገኘው።
በሰላም ሚኒስቴር የህግ ማስከበር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ፍሬአለም ሽባባው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተዘግተው የነበሩትን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንደገና ለማስጀመር የፖሊስ አባላት ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ወይዘሮ ፍሬአለም በሽታው እየተስፋፋ ከመሆኑም አኳያ ጥንቃቄ ማድረግ እና ግጭቶች እንዳይከሰቱ የሰራዊት አባላት ጠንክረው በመስራት የመማር ማስተማሩን ሂደት ሰላማዊ እንዲሆን ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ማሳሰባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የፖሊስ አባላት ጸጥታ ማስከበር ብቻ ሳይሆን የሚፈጠሩ ስህተቶችን ወደ ትምህርት በመቀየር መካሪም አስተማሪም መሆን እንዳለባቸው ተናግረዋል።

The post በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚሰማሩ የፖሊስ አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply