በኪረሞ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል የተገደሉ አማራዎች አስከሬን በየቦታው ወድቆ እየተገኘ ነው፤ በኪረሞ ከተማ ብቻ በ3 ቀናት ውስጥ በርካታ አማራዎችን መግደሉ ይታወቃል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

በኪረሞ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል የተገደሉ አማራዎች አስከሬን በየቦታው ወድቆ እየተገኘ ነው፤ በኪረሞ ከተማ ብቻ በ3 ቀናት ውስጥ በርካታ አማራዎችን መግደሉ ይታወቃል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 13 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በኪረሞ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል የተገደሉ አማራዎች አስከሬን በየቦታው ወድቆ እየተገኘ ስለመሆኑ የሚገልጹት የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) የመረጃ ምንጮች ይጠብቁናል በሚል በቤት ውስጥ የነበሩ ሴቶችንና ህጻናትን ሳይቀር በጭካኔ መግደላቸውን ጠቁመዋል። ህዳር 13/2015 በኪረሞ ከተማ ጥና ተፈሪ ቴሌ አካባቢ የ4 አማራዎች አስከሬን ወድቆ ተገኝቷል። 1) እባቡ ካሳ፣ 2) ካሳሁን አብዬ እና 3) ስመኘው ዘውዱ የተባሉ ሰዎች አስከሬን ወድቆ ተገኝቷል። የ4ኛውን ሰው ስም ለጊዜው ለማወቅ አልተቻለም። ህዳር 10/2015 በኦሮሚያ ልዩ ኃይል በኪረሞ በአማን አምባ እና በወሎ ሰፈር አካባቢ ብቻ ብዙ ሰዎች ተገድለዋል። በኪረሞ ከተማ ህዳር 9፣10 እና 11/2015 በግፍ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከተገደሉት መካከል:_ 1) ኡስማን ካሳው፣ 2) ሼህ ፋቲ አሊ፣ 3) አዲሱ ሞንጋሴ፣ 4) ካሳሁን አብዬ፣ 5) ቄስ ስመኘው ዘውዱ፣ 6) አስቻለው ይሁኔ፣ 7) መሀመድ ከማል (የ4 ልጆች አባት)፣ 😎 ደሳለኝ ዳውድ እና 9) ካሳ ከበደ፣ 10) ኡስማን አሊ የተገደሉ ሲሆን 11) ደምሴ፣ 12) ሞላ፣ 13) መሀመድ፣ 14) ቀሬ እና 15) ምህረት አሞኜ፣ 16) ንብረት አሞኜ_(አረንጓዴ፣ቢጫ፣ቀይ ባንዴራ በራሱ ላይ ጠምጥሞ አገኘነው በሚል ነው የገደሉት) 17) መኩሪያው አበረ፣ 18) ሀብታሙ ጫኔ፣ 19) አለቤ ወዳጅ እና ሌላ 20) አንድ ስሙ ያልታወቀ አማራም መገደላቸው ተገልጧል። ፍቃዱ ሁንዴ የተባለው የኪረሞ ወረዳ አስተዳዳሪ፣ወንዴ ኦልጅራ የተባለ የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ ከእነ ግብረ አበሮቹ ተጠያቂ ናቸው ተብሏል። እነዚህ አመራሮች በጥላቻ ታውረው 260 በዘር ፍጅት ወንጀል በመከላከያ አዛዥ በእነ ሻለቃ ደረሰ የተያዙ ኦነጎችን በነጻ በመልቀቅ ከብት ሲጠብቁ በማንነታቸው ብቻ የያዟቸውን ከ26 በላይ አማራዎችን ወደ ነቀምት በመውሰድ በሀሰት ለማስፈረድ እየሰሩ ነበር ተብሏል። በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ማንነት ተኮር ጥቃት የተነሳም ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ብቻ 52 ሽህ ተፈናቃዮች ወደ ሀሮ አዲስ ዓለም ቀበሌ ገብተው መጠለያ ባለመኖሩ በመናህሪያ፣ በት/ቤት እና በየጎዳናው በተበታትነው በከፍተኛ ችግር እየተቃዩ ነው ተብሏል። ፍቃዱ ወንዴ የተባለው የኪረሞ ዋና አስተዳዳሪ የተፈጠረውን ችግር በእርቅ እንፍታው ሲባል “እናንተን በእግራችሁ አማራ ክልል ሳናደርስ የምናደርገው ድርድር የለም” በማለት የለዬለት የጽንፈኝነት ንግግር ከመናገሩም በላይ በተግባር በአማራ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት እና ዝርፊያ አስተባብሯል በሚል ተወቅሷል፤ በውጭ የሚኖሩ ባለሃብቶችም በጥቃቱ በገንዘብ ድጋፍ እየተሳተፉ ነው ተብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply