You are currently viewing በኪረሞ ወረዳ ሀሮ አዲስ ዓለም ላይ በቡድን መሳሪያ የታገዙ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ኮማንዶዎችና ኦነግ ሸኔ የተባለው የሽብር ቡድን በፈጸመው ጥቃት ከ60 ያላነሱ አማራዎች መገደላቸው ተነገረ፤ አ…

በኪረሞ ወረዳ ሀሮ አዲስ ዓለም ላይ በቡድን መሳሪያ የታገዙ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ኮማንዶዎችና ኦነግ ሸኔ የተባለው የሽብር ቡድን በፈጸመው ጥቃት ከ60 ያላነሱ አማራዎች መገደላቸው ተነገረ፤ አ…

በኪረሞ ወረዳ ሀሮ አዲስ ዓለም ላይ በቡድን መሳሪያ የታገዙ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ኮማንዶዎችና ኦነግ ሸኔ የተባለው የሽብር ቡድን በፈጸመው ጥቃት ከ60 ያላነሱ አማራዎች መገደላቸው ተነገረ፤ አድራሻቸው የጠፉ ብዙ ናቸው ተብሏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 16 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ እና ሆሮ ጉድሩ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት አራት ዓመታት በተለያዩ ጊዜያት በአማራ ላይ የለየለዬት የዘር ፍጅት እየተፈጸመ ነው። ይህንን የጅምላ ፍጅት የሚያስቆም እና በቡድን መሳሪያ ታግዘው የሚጨፈጭፉ ኦነጋዊያንን በህግ ተጠያቂ የሚያደርግ አካል አልተገኘም። የኦሮሚያ ክልል መንግስት ስምሪት የሰጠው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ኮማንዶ ጭምር እንዲሁም ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና አጋሮቻቸው ጋር በመቀናጀት አሁንም በማንነታቸው ብቻ ለይተው አማራዎችን በተደጋጋሚ እያጠቁ ነው። ከምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞን፣ወዴሳ ዲማን፣ ሀሮ አዲስ ዓለምን፣ አንገር ጉትንን፣ አንዶዴን፣ በሳሲጋ ጽጌን፣ ሀያ አራት፣ ኡኬ ቀርሳን፣ ሊሙን እንዲሁም ከሆሮ ጉድሩ ጃርዴጋን እና አካባቢውን በተለይም ከህዳር ወር 2015 ጀምሮ በጦርነት በማመስ እና በማውደም ላይ የሚገኘው ይህ መንግስት መር ጥምር ኃይል ታህሳስ 14/2015 ዳግም በሀሮ አዲስ ዓለም እና በወዴሳ ዲማ የወረራ ጦርነት ከፍቶ ጉዳት አድርሷል። ጭካኔ በተሞላው ጥቃቱም እንደ አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ምንጭ ከሆነ በሀሮ አዲስ ዓለም ብቻ ከ60 ያላነሱ አማራዎች ተገድለዋል። እንደአብነትም ህጻናትንና ሴቶችን ሲከላከሉ የነበሩ ከ8 በላይ አርሶ አደሮች ስለመገደላቸው አውቄያለሁ ያለው የዐይን እማኝ በተጨማሪም ታህሳስ 14/2015 ከ10 በላይ አማራዎች መቀበራቸውን አውቄያለሁ ብሏል። ከመካከላቸውም 3 ህጻናት እና 2 እናቶች ታህሳስ 14/2015 ስርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል፤ አድራሻቸው የጠፉት ብዙ ስለመሆናቸውም ገልጧል። ታህሳስ 14/2015 በሀሮ አዲስ ዓለም ከተገደሉት መካከልም:_ 1) ሙሳ ሞላ፣ 2) ሁሴን ጌታሁን የተባሉ ቤተሰቦቹ እና ሌሎች 6 የአካባቢው ነዋሪዎች ስለመገደላቸው መረጃ ማግኘቱን ሌላኛው ምንጫችን ተናግሯል። ሌላኛዋ ተፈናቅላ በጉራጌ ዞን የምትገኝ አማራ ደግሞ 2 ቤተሰቦቿ እንደተገደሉባትና ሌሎች የቆሰሉም እንዳሉ ለአሚማ ተናግራለች። ዲሽቃ፣ ብሬንና እና ስናይፐር ይዘው ለጭፍጨፋ ወደ ሀሮ አዲስ ዓለም የገባው የኦሮሚያ ክልል መንግስት ያሰማራው ጦር፣ ልዩ ኃይሉ ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ጋር በመቀናጀት በአራት አቅጣጫ በከፈቱት ጥቃት ከ60 በላይ አማራዎች ስለመገደላቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ታህሳስ 14/2015 ከንጋት ጀምሮ በሀሮ አዲስ ዓለም እና ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ደግሞ በወዴሳ ዲማ የወረራ ጦርነት ከፍቶ በመዋሉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አማራዎች ተገድለዋል። ከተገደሉትም መካከል ህጻናትና ሴቶች ይገኙበታል፤ አድራሻቸው የጠፉም ብዙ ናቸው ተብሏል። ከህዳር 9/2015 ጀምሮ ለ4 ዙር በኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ በኦነግ ሸኔ እና አጋሮቻቸው ኪረሞ ላይ በተፈጸመው ጥቃት የቆሰሉ በርካቶችን ጨምሮ አሁን ደግሞ ታህሳስ 14/2015 የቆሰሉትን የህክምና ባለሙያ እና ተቋምም ስለሌለ የብዙዎች ህይወታቸው እያለፈ ስለመሆኑም ተገልጧል። አሚማ መረጃውን የበለጠ እያጣራ ወደእናንተ የሚያደርስ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply