በኪረሞ ወረዳ በእስር ላይ የሚገኙ የአማራ ተወላጆችን ብቻ በመለየት ወደ ነቀምት ለመውሰድ የተደረገው ሙከራ በህዝቡ ዘንድ ቅሬታ አስነሳ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 9 ቀን 201…

በኪረሞ ወረዳ በእስር ላይ የሚገኙ የአማራ ተወላጆችን ብቻ በመለየት ወደ ነቀምት ለመውሰድ የተደረገው ሙከራ በህዝቡ ዘንድ ቅሬታ አስነሳ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 9 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በኪረሞ ወረዳ በተለያዩ ጊዜያት ተይዘው በእስር ላይ የሚገኙ የአማራ ተወላጆችን ብቻ በመለየት ህዳር 9/2015 ከጠዋቱ 1 ሰዓት ጀምሮ ወደ ነቀምት ለመውሰድ የተደረገ ሙከራ በህዝቡ ዘንድ ቅሬታ አስነስቷል። በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ ጉዲና ጅሬኛ/ቦቃ በተባለ አካባቢ 22 አማራዎችን በግፍ ያረዱ፣ ያሳረዱ እና አማራዎችን ተቀጥቅጠው እንዲገደሉ ያደረጉ አካላትን ጨምሮ ሁሉም በሚባል አግባብ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ እስረኞች ከሰሞኑ ከእስር ተፈተዋል። ከተፈቱት መካከልም እንደአብነት:_ 1) አቶ ረጋሳ ቀኑ፣ 2) አቶ ይርባ በየነ፣ 3) አቶ ደሳለኝ ያደታ፣ 4) አቶ መገርሳ ጣባ እና 5) አቶ ሹማ ባንጉ የተባሉ በጉዲና ጅሬኛው የመስከረም 8/2014ቱ አማራ ተኮር ጥቃት እጃቸው ያለበት ስለመሆናቸው ተገልጧል። ሆንተብሎ ጥቃቅን ምክንያት እየተፈለገላቸው በተለያዩ ጊዜያት የታሰሩ አያሌ የአማራ ተወላጆች ግን ከኦሮሞ ተወላጆች ተለይተው ስለምን በእስር እንዲቆዩ ተደረገ የሚለው የህዝቡ ቅሬታ ነው። ይባስ ብሎ ህዳር 9/2015 ከጠዋቱ 1 ሰዓት ጀምሮ በእስር ላይ ያሉ የአማራ ልጆችን ሰብስበው ወደ ነቀምት ለመውሰድ ሙከራ ማድረጋቸው ቅሬታ አስነስቷል። መንገድ ላይም ያለምንም ወንጀል ሰበብ እየፈጠራችሁ ያሰራችኋቸውን ስለምን ልጆቻችንን ወደ ነቀምት ለይታችሁ ትወስዳላችሁ በሚል በተነሳ ተቃውሞ መስተዳድሩ ወደ ኪረሞ ፖሊስ ጣቢያ ተመልሰው እንዲገቡ ማድረጉ ተሰምቷል። ነገር ግን መፈታት የሚገባቸውን ልጆቻችንን አሁንም አሳልፈው ወደ ነቀምት ላለመውሰዳቸው እርግጠኛ አይደለንምና የሚመለከተው አካል ይህን የለዬለት ዘር ተኮር ጥቃት በማስቆም በአስቸኳይ የግፍ እስረኞችን እንዲፈታልን እንጠይቃለን ሲሉ ጥሪ አድርገዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply