You are currently viewing በኪረሞ ወረዳ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ለአማራ ቤት እና ሱቅ ያከራዩ ኦሮሞዎችን በማስፈራራቱ 8 በማንነታቸው አማራ የሆኑ ባለሱቆች ያለማስጠንቀቂያ ከቤታችን ልቀቁ መባላቸው ተገለጸ። አማራ ሚዲያ…

በኪረሞ ወረዳ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ለአማራ ቤት እና ሱቅ ያከራዩ ኦሮሞዎችን በማስፈራራቱ 8 በማንነታቸው አማራ የሆኑ ባለሱቆች ያለማስጠንቀቂያ ከቤታችን ልቀቁ መባላቸው ተገለጸ። አማራ ሚዲያ…

በኪረሞ ወረዳ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ለአማራ ቤት እና ሱቅ ያከራዩ ኦሮሞዎችን በማስፈራራቱ 8 በማንነታቸው አማራ የሆኑ ባለሱቆች ያለማስጠንቀቂያ ከቤታችን ልቀቁ መባላቸው ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 4 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና ተባባሪዎቹ በአማራዎች ላይ ይፋዊ ጦርነት በመክፈት ጥቃት መፈጸሙና እየፈጸመ መሆኑ ይታወቃል። ከ327 በላይ አማራዎችን ነዋሪዎች እንደሚሉት ከካሃዲ የመስተዳድር አካላት ጋር በመናበብ በመኪና እየተጫኑ የመጡ የሽብር ቡድኑ አባላት በሶስት ቀናት ብቻ በመርጋ ጅሬኛ፣ ስኒ ዶሮ፣ አሹ እና በቦቃ ቀበሌዎች መጨፍጨፋቸው ተወስቷል። ዛሬም በንጹሃን ላይ የጀመረውን ግልጽ ጦርነት እያስቀጠለ ያለው የሽብር ቡድኑ ከኢትዮጵያዊያን ወግና ባህል ተቃራኒ የሆኑ የበዙ የነውር ድርጊቶችን መፈጸሙ በተለያዩ ጊዜያት በአሚማ ተዘግቧል። በቡድን ህጻናትንና ሴቶችን ከመድፈር ጀምሮ ንጹሃንን ማረድ፣ ሰልፊ እየተነሳ ነውር ድርጊቱን በኩራት ማሳየት፣ አህያ እስከ ማረድ ብሎም ከአማራ ጋር አትገበያዩ ብሎ እስከመከልከል የዘለቀ የወንጀል ድርጊት ፈጽሟል። አሚማ ከኪረሞ ለማጣራት እንደሞከረው ከወራት በፊት መ/ር ከበደ ኪትል እና መርጋ ኪትል የተባሉ የኦሮሞ ተወላጆች በሽብር ቡድኑ ጫና ምክንያት በቤታቸው የነበረን አማራ እንዲለቅ አድርገዋል። በተመሳሳይ ጥቅምት 3 ቀን 2014 ከቀኑ 12 ሰዓት አካባቢ ለአማራ ያከራዩትን ሱቅ በአስቸኳይ እስካላስለቀቁ ድረስ እርምጃ እንወስዳለን የተባሉ በኪረሞ የ01 ቀበሌ ነዋሪ 8 አማራዎችን ዛሬ ጥቅምት 4 ቀን 2014 ከረፋድ ጀምሮ ያለቅድመ ማስጠንቀቂያ ከተከራዩበት ሱቅ እንዲለቁ ማሳሰባቸው ተሰምቷል። ይህ አካሄድ ብዙዎችን ቅር ማሰኘቱ ተገልጧል። ከተማ አስተዳደር ሄደው ሲጠይቁም ከእኛ ጋር ውሉ ስላላስገባችሁ አይመለከተንም ስለመባላቸው ለአሚማ የደረሰው መረጃ አመልክቷል። ከአማራ ጋር ይቀራረባሉ፣ ይግባባሉ፣ ለምን ብለው ይጠይቃሉ የሚባሉ የኦሮሞ ተወላጆችም የጥቃቱ ሰለባ እንደሚሆኑ ተነግሯል። እንደአብነትም አምሳ አለቃ ምስጋናው ገለታው የተባሉ የኦሮሞ ሚሊሻ ይህን ሀገርና ህዝብን ለውስብስብ ፈተና የዳረገውን ዘረኛ አሰራር ባለመደገፋቸው ነሃሴ 27 ቀን 2013 ዓ/ም በ87 ዚንጎ ቆርቆሮ የሰሩትን የመኖሪያ ቤታቸውን ነዳጅ እያርከፈከፉ አቃጥለውባቸዋል፤ መጨረሻ ላይም የተገደሉ መሆናቸው ተሰምቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply