በኪረሞ ወረዳ ከዋስቲ ቀበሌ ተሻግረው የመጡ የአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ቡድን ባጊን ቀበሌ ባሉ አማራዎች ላይ ጥቃት ከፍተው እንደነበር ተገለጸ ህዳር14/2014/አሻራ ሚዲያ / በምስራቅ ወለጋ…

በኪረሞ ወረዳ ከዋስቲ ቀበሌ ተሻግረው የመጡ የአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ቡድን ባጊን ቀበሌ ባሉ አማራዎች ላይ ጥቃት ከፍተው እንደነበር ተገለጸ ህዳር14/2014/አሻራ ሚዲያ / በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ ባጊን ቀበሌ ላይ ህዳር 12 ቀን 2014 ከንጋት ጀምሮ በአማራዎች ላይ የተከፈተው ተኩስ ከፍተው እንደነበር ተገልጧል የአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ቡድን አባላትና የጥፋት ተባባሪዎቹ ከዋስቲ ቀበሌ ተሻግረው በመምጣት ነው ባጊን ቀበሌ በሚኖሩ አማራዎች ላይ ተኩስ የከፈቱት። በርካታ ቤቶች በሽብር ቡድኑ እየተቃጠሉ መሆኑን የተናገሩት ምንጮች ህዳር 10 ቀን 2014 በኪረሞ ወረዳ ባጊን ቀበሌ ሰጊ አካባቢ አቶ መልካሙ በላይ እና ባለቤታቸውን ወ/ሮ እንዳሻዋ ሰጠኝን በግፍ ገድለዋል፤ ትልቅ ሴት ልጃቸውንም አግተው ወስደዋል ሲሉ አስተውሰዋል። ይህን ተከትሎም በተ…ደረገው የአጸፋ የተኩስ ልውውጥም በርካታ ሚሊሾች ቆስለዋል ብለዋል። ነዋሪዎቹ የሚመለከተው የመንግስት አካል በአስቸኳይ እንዲደርስላቸው በሚል ጥሪ ካቀረቡ ቢቆዩም ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ድረስ ግን አንድም የደረሰላቸው አካል እንዳልተገኘ ገልጸዋል። በተመሳሳይ በጊዳ አያና ወረዳ ዶሮ በራ ቀበሌ የሚገኙ አማራዎች በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና የጥፋት አጋሮቹ ተደጋጋሚ ጥቃት የተነሳ ዓመቱን ሙሉ የደከምንበትን አዝመራ ለመሰብሰብ አልቻልንም ሲሉ አማረዋል። የመንግስት አካልም ደርሶ ሊታደገን አልቻለም ያሉት የዶሮ በራ ቀበሌ ነዋሪዎች የሽብር ቡድኑ ያደራጃቸው ዘራፊዎች የአማራውን ቤት በመለየት እየዞሩ በመዝረፍና በማቃጠል ላይ ይገኛሉ ሲሉም አክለዋል

Source: Link to the Post

Leave a Reply