በኪረሞ ወረዳ ከጊዳ አያና የመጣ አዲስ የታጠቀ ኃይል በአማራ ሚሊሾች እና ነዋሪዎች ላይ በከፈተው ጥቃት በርካታ ሰዎች ተገደሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 10 ቀን 2015 ዓ/ም…

በኪረሞ ወረዳ ከጊዳ አያና የመጣ አዲስ የታጠቀ ኃይል በአማራ ሚሊሾች እና ነዋሪዎች ላይ በከፈተው ጥቃት በርካታ ሰዎች ተገደሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 10 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ህዳር 9/2015 የአማራ ተወላጅ የሆኑ የግፍ እስረኞችን ከኪረሞ አፍነው ወደ ነቀምት ለመውሰድ የተደረገው ሙከራ አየር ማረፊያ አካባቢ በተነሳ የህዝብ ተቃውሞ መክሸፉ ይታወቃል። በሀገር ሽማግሌዎች እና በሀይማኖት አባቶች ለማግባባት ቢሞከርም መስተዳድሩ ፍቃደኛ ከመሆን ይልቅ ባሰማራው ልዩ ኃይል አማካኝነት ጥያቄ ባቀረቡት ላይ ተኩስ በመክፈት ጉዳት በማድረሱ የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል። ይህን ተከትሎም የኪረሞ ወረዳ ከጊዳ አያና ወረዳ በአንድ ሲኖትራክ የተጫነ በዩኒፎርሙ የተለዬ አዲስ የታጠቀ ኃይል ወደ ኪረሞ በማስመጣት መሀል ከተማ ላይ ተኩስ እንዲከፈት አድርጓል። ያስመጡት ኃይልም ከተማ ላይ ያገኘውን አማራ እየተኮሰ መግደል መጀመሩን ተከትሎ ሚሊሾችን ጨምሮ ከ35 በላይ አማራዎች እንደተገደሉ ተመልክተናል ብለዋል ወደ ጫካ የሸሹ የዐይን እማኞች። ተኩሱ ማየሉን እና ወደ ከተማ መግባቱን ተከትሎ በፖሊስ ጣቢያው አካባቢም ተኩስ በመከፈቱ ነግፍ እስር ላይ የነበሩ አማራዎችን ጨምሮ ከ200 በላይ እስረኞች የተለቀቁ መሆናቸው ተነግሯል። የኪረሞ ወረዳ ከጊዳ አቅጣጫ ካስመጡት አዲስ እና የተለዬ ኃይልም በርካቶች መገደላቸው ተሰምቷል። በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ በተለይም ከረፋዱ 4 ሰዓት እስከ ቀኑ 8 ሰዓት ድረስ የቆዬ ተኩስ እንደነበር ተገልጧል። አመሻሹንም 6 መኪና ሙሉ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ወደ ኪረሞ እየተጓዘ መሆኑን ሰምተናል የሚሉት የአሚማ ምንጮች አማራዎችን ሊያጠቁ ይችላሉ የሚል ከፍተኛ ስጋት አድሮባቸዋል። በመጨረሻም በየጫካው እየተሳደዱ የሚገኙ አማራዎች ከነቀምት መከላከያ መጥቶ እንዲታደጋቸው ጥሪ አቅርበዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply