You are currently viewing በኪረሞ ወረዳ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና አጋሮቹ በከፈቱት ጦርነት 6 አማራዎች ሲገደሉ የቆሰሉ ስለመኖራቸው ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ህዳር 26 ቀን 201…

በኪረሞ ወረዳ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና አጋሮቹ በከፈቱት ጦርነት 6 አማራዎች ሲገደሉ የቆሰሉ ስለመኖራቸው ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 26 ቀን 201…

በኪረሞ ወረዳ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና አጋሮቹ በከፈቱት ጦርነት 6 አማራዎች ሲገደሉ የቆሰሉ ስለመኖራቸው ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 26 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና አጋሮቹ በከፈቱት ጦርነት 6 አማራዎች ሲገደሉ የቆሰሉ ስለመኖራቸው ነው ነዋሪዎች ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) የተናገሩት። ህዳር 24/2015 ረፋድ ላይ ጀምሮ እስከ ቀኑ 10 ሰዓት በቆዬው ጥቃት ህጻናት እና ሴቶችን ለማሸሽ እና ራሳቸውን ለመከላከል ሲሞክሩ የነበሩ 6 አማራዎች ሲገደሉ የቆሰሉ መኖራቸውንም የአሚማ የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል። ከተገደሉት መካከልም 0937950358 የሆነውን የአቶ ንጉስ ደባልቀውን የሞባይል ስልክን በመጠቀም እየተሳደቡ እና ገና እንጨርሳችኋለን እያሉ ቤተሰብ እና የአቶ ንጉስ ደባልቀውን ጓደኞች እያስፈራሩ መሆናቸው ተገልጧል። ህዳር 24/2015 ከተገደሉት መካከልም:_ 1) አደም ካሳው፣ 2) ንጉስ ደባልቀው እና ሌሎች በስም ምንጫችን ያላወቃቸው 4፣ በድምሩ 6 አማራዎች በኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ፣ የስርዓት ጋሻ (ጋቼና ሲርና)፣ ሽምቅ ተዋጊ (ሪጴሎላ) እና በሌሎች የከባቢ ኃይሎች ቅንጅት ተገድለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply