በካሃዲው ትሕነግ ላይ የሚወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃ በዘገዬ ቁጥር ቡድኑ መልሶ ለመደራጀት ብሎም በንፁሃን ላይ ጉዳት ለማድረስ እድል እየሰጠው መሆኑን አስተውለናል ሲሉ የጠለምት አማራ ማ…

በካሃዲው ትሕነግ ላይ የሚወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃ በዘገዬ ቁጥር ቡድኑ መልሶ ለመደራጀት ብሎም በንፁሃን ላይ ጉዳት ለማድረስ እድል እየሰጠው መሆኑን አስተውለናል ሲሉ የጠለምት አማራ ማ…

በካሃዲው ትሕነግ ላይ የሚወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃ በዘገዬ ቁጥር ቡድኑ መልሶ ለመደራጀት ብሎም በንፁሃን ላይ ጉዳት ለማድረስ እድል እየሰጠው መሆኑን አስተውለናል ሲሉ የጠለምት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ መ/ር ፀጋዬ እሸቴ ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 14 ቀን 2013 ዓም አዲስ አበባ ሸዋ መንግስት ለጠለምት ትግል በሎጅስቲክና በጦር ሀይል የሰጠውን አነስተኛ ትኩረት ገምግሞ ይበልጥ እንዲያጠናክር ያሳሰቡት የጠለምት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ መ/ር ፀጋዬ እሸቴ ናቸው። መ/ር ፀጋዬ ሲቀጥሉ ምህረት ለሚገቡት እድል ለመስጠት በሚል ትግሉ በዘገዬ ቁጥር የጠላት ሀይል እንደገና እንዲደራጅ ብሎም በአንዳንድ አካባቢዎችም በንፁሃን ላይ ዝርፊያ፣ እንግልትና መሰል ጉዳት እንዲያደርሱ እድል እየሰጣቸው መሆኑን ተመልክተናል ብለዋል። ከሰሞኑ በጠለምት ግንባር ሰቆጣ የተባለ አካባቢን በዛሬው እለት ደግሞ የወገን ኃይል ተቆርጦ የቀረውን እና በአካባቢው መሽጎም ጉዳት እያደረሰ ያለውን ተስፋፊ ቡድን በመምታት የዲማ ወረዳን ነጻ ማድረጉ ተገልጧል። በመጨረሻም መንግስት በጠለምት ግንባር በኩል ያለውን ሀይሉን አጠናክሮ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመ ያለው የትሕነግ ቡድን ዳግም እንዳያንሰራራ አድርጎ ህግ የማስከበር እርምጃውን መውሰድ አለበት ብለዋል_መ/ር ፀጋዬ እሸቴ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply