በኬኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የወታደራዊ ከፍተኛ መኮንን የሆኑት ብርጋዴር ጀኔራል ኪዱ ፍርድቤት ቀረቡ

በኬኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የወታደራዊ ከፍተኛ መኮንን የሆኑት ብርጋዴር ጀኔራል ኪዱ ፍርድቤት ቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የወታደራዊ ከፍተኛ መኮንን ብርጋዴር ጀኔራል ኪዱ አለሙ ፍርድቤት ቀረቡ፡፡
ተጠርጣሪው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት አንደኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀረቡ ሲሆን መርማሪ ፖሊስም የሰራቸውን የምርመራ ስራዎች ለችሎቱ አስረድቷል፡፡
ተጠርጣሪው ኬኒያ ሆነው የኦነግ ሸኔ አባላትን ሲመለምሉና ስልጠናም ሲሰጡ እንደነበረ ለችሎቱ የገለፀው መርማሪ ፖሊስ ከህወሓት የፀረሰላም ቡድኖች ጋርም ተልዕኮ ተቀብለው በዚያው በኬኒያ ቅስቀሳ ሲያደርጉ እንደነበር በማስረጃ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡
በመኖሪያ ቤታቸው ባደረኩት ምርመራ የተለያዩ ከፍተኛ የገንዘብ መጠን ያላቸው የባንክ ደብተሮች፣ ኤሌክትሮኒክሶች እንዲሁም በእጃቸው የተገኙ ሞባይሎችን ለቴክኒክ ምርመራ ለሚመለከተው አካል ልኬአለሁ ብሏል::
ቀረኝ ባላቸው የምርመራ ስራዎቹ የእሳቸውንና የምስክር ቃል መቀበል፣ በትግራይ በተለያዩ ቦታዎች በተፈፀሙ ወንጀሎች የአስከሬን ምርመራ ውጤት ማስመጣት እና ሌሎች ሰራዎችን ለማከናወን ተጨማሪ 14 ቀናት ያስፈልገኛል ብሏል፡፡
የተጠርጣሪ ጠበቃም በህገ መንግስቱ አንቀፅ 19 ንዑስ ቁጥር 3 ጊዜ ቀጠሮን በተመለከተ በቂ ምክንያት ሊኖር ይገባል ነው የሚለው ሲል ተጨማሪ የጊዜ ጥየቃን ተቃውሟል፡፡
የአስከሬን ምርመራን በተመለከተ እሳቸው ያላቸው ግንኙነት የለም፣ ስለዚህም ተጨማሪ ጊዜ ሊጠየቅ አይገባም፤ ቃላቸውንም እስካሁን መቀበል ይገባው ነበር ሲል በዋስ ወጥተው ከውጭ ቢከታተሉ ማስረጃዎችን ሊያሸሹ አይችሉም ሲል ተከራክሯል፡፡
ብርጋዴር ጀነራል ኪዱ በበኩላቸው የአስም ህመምተኛ መሆናቸውን ገልፀው ከመጋቢት 2011 አስከ ህዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም በኬኒያ ኤምባሲ በስራ ላይ ነበርኩኝ፤ ተመለሱ ሲባል ነው የመጣሁት ወንጀል ቢኖርብኝ በዚያው መጥፋት እችል ነበር፤ በመኖሪያ ቤቴ 2 የባንክ ደብተርና ለስራ የምጠቀምባቸው የራሴ ሞባይሎች ናቸው የተገኙት ፍርድቤቱም በዋስ እንዲለቀኝ እጠይቃለሁ ሲሉ አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡
ጉዳዩን ያየው ፍርቤትም በዋስ ቢወጡ ምርመራውን ሊያደናቅፉ ይችላሉ ሲል 13 ተጨማሪ ቀናትን ለፖሊስ ፈቅሷል፡፡
በታሪክ አዱኛ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በኬኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የወታደራዊ ከፍተኛ መኮንን የሆኑት ብርጋዴር ጀኔራል ኪዱ ፍርድቤት ቀረቡ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply