በኬንያ ከፍተኛ ተቃዉሞ መቀስቀሱ ተነገረ፡፡
ተቃውሞውም በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች እና ራይላ ኦዲንጋን በሚደግፉ የድጋፍ ሰልፈኞች መካከል መሆኑም ታዉቋል፡፡
በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ቢያንስ አንድ ሰው በጥይት ሲመታ ብዙዎች መቁሰላቸውን ቢቢሲ አፍሪካ ዘግቧል፡፡
በኬንያ ያለፈው ምርጫ ውጤት ተሰርቋል የሚሉት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የሆኑት ራይላ ኦዲንጋ፣ በአገር አቀፍ ደረጃ ተቃውሞ እንዲካሄድ ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው፡፡
ለተቃውሞው ዋነኛ ማነሻ የሆው ደግሞ አምስት ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት የተወዳደሩት ኦዲንጋ ፣ መንግስት የኬንያውያንን የኑሮ ውድነት ለመቅረፍ ምንም አይነት እርምጃ አልወሰደም ብለው መክሰሳቸው አንዱ ነው፡፡
ፖሊስ የኦዲንጋ ንግግርን ተከትሎ ሰላማዊ ሰልፍ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ እና በኮንቮይ በወጡ ዜጎች ላይ አስለቃሽ ጭስ መተኮሱን የቢቢሲ ዘገባ አመልክተዋል።
በዋና ከተማዋ ወደሚገኙ ከፍተኛ የመንግስት መስርያ ቤቶች የሚወስዱ መንገዶች እና የፕሬዚዳንቱ ይፋዊ መኖሪያ ቤት ተዘግቷልም ነው የተባለው።
ቢቢሲ አፍሪካ አይን እማኞችን ምንጭ አድርጎ እንደዘገበው ሰልፈኞች በፖሊስ ላይ ድንጋይ ሲወረውሩ እና በርካቶች ለእስራት መዳረጋቸውን ዘግቧል፡፡
በረድኤት ገበየሁ
መጋቢት 11 ቀን 2015 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን