በኬንያ የአልሸባብ ሃይሎች በከፈቱት ጥቃት 6 ሰዎች ሞቱ

በኬንያ የአልሸባብ ሃይሎች በከፈቱት ጥቃት 6 ሰዎች ሞቱ

በኬንያ የወደብ ከተማ በሆነችው ላሙ (Lamu County) አካባቢ የአልሸባብ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት 6 የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸው ከከተማዋ ኮሚሽነር ሰምቻለሁ ሲል ሲጂቴን ከደቂቃዎች በፊት ዘግቧል፡፡

ዘገባው አክሎ እንደገለጸው ከሆነ ታጣቂዎቹ በርካታ ቤቶችን ማቃጠላቸውንም አትቷል፡፡

የአሸባሪው የአልሸባብ ሃይሎች ሰዎችን የገደሉትም ጥይት በመተኮስ፤ በድብደባ እና ሰዎች ቤታቸው ውስጥ እንዳሉ በማቃጠል እንደሆነና እጅግ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ስለመፈጸሙ ነው ያስታወቀው፡፡

ከጥቃቱ በኋላ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ በከተማዋ የደህንነት አባላት የማጣራት ስራው መጀመሩንም ዘገባው አክሎ አስታውቋል፡፡

ጅብሪል መሀመድ
ታህሳስ 25 ቀን 2014 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply