በክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ሥም በድሬደዋ ከተማ ፓርክ ተሰየመ

ሐሙስ ሐምሌ 14 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ በተወለደባት ድሬደዋ ከተማ በዛሬው ዕለት በሥሙ ፓርክ ተሰይሟል::

በአርቲስቱ ሥም በተሰየመው ፓርክ የምርቃት ሥነ ሥርዓት ላይም የድሬዳዋ ከንቲባ ከድር ጁሃርን ጨምሮ ክቡር ዶክተር አሊ ቢራና ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች እንግዶች መገኘታቸውን የከተማዋ አስተዳደር ኮምዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

አርቲስት አሊ ቢራ የሙዚቃ ሥራን በ1954 እንደጀመረ የሚነገር ሲሆን፤ ከኦሮምኛ በተጨማሪ በአማርኛ፣ በሱማሊኛ፣ በአፍርኛ፣ በሐረሪ እና በአረብኛ ቋንቋዎች የሙዚቃ ሥራዎችን ሰርቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply