በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ሌንጮ ሰፈር ማርያም አካባቢ ቤታቸው የፈረሰባቸው ነዋሪዎች አቤቱታ እንዳያቀርቡ ከፍተኛ ጫና እየደረሰባቸው መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 17 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ሁለት እና ሶስት ሆኖ ለሻይ ቡናም ሆነ ለሌላ ጉዳይ መቀመጥ አልቻልንም ሲሉ ተጎጅዎች አማረዋል። ለእምባ ጠባቂ ተቋም የካቲት 16/2015 አቤቱታ ብናቀርብም “ኦሮሚያ ላይ ሂዳችሁ ጩኹ፤ እናንተ በቀጥታ ወደ እኛ መምጣት የለባችሁም” በማለት ደብዳቤያቸውን አንቀበልም ብለው መልሰውናል። አቤቱታውን አልቀበላቸው ሲሉም “ተቋሙ እምባ ጠባቂ ሳይሆን እምባ አፍሳሽ ነው ሊባል የሚገባው” በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል። “ኦሮሚያማ ለአቤቱታ አንሄድም፤ ማን የችግሩ ፈጣሪ ሆኖ ነው ወደ ኦሮሚያ ሄደን አቤቱታ የምናቀርበው፤ አንሄድም” የሚል አስተያየት ተሰጥቷል። “እምባ ጠባቂም በሉት እምባ አፍሳሽ፣ ምንም በሉት ምን ከፈለጋችሁት መሄድ ትችላላችሁ” የሚል ምላሽ ነው እምባ ጠባቂ ከተባለው ተቋም የተሰጠን ምላሽ ሲሉ አውግዘዋል። ስድስት የሚሆኑ አቤቱታ አቅራቢዎች ሁኔታው አሳዛኝ መሆኑ ተገልጧል። የካቲት 17/2015 በአለም ባንክ አካባቢ ያሉ ተጎጅዎችን አቤቱታ ለማቅረብ እየተንቀሳቀሳችሁ ነው በሚል በኦሮሞ የደህንነት አካላት አፈና ሊፈጸምባቸው ሲል ሸሽተው ማምለጣቸው ተገልጧል። ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰላይ ኃይል በማስገባት ግለሰቦችን ሁሉ ሳይቀር በመሰለል ላይ ተጠምደዋል፤ መቀመጫ እና መቆሚያ ነስተውናል ሲሉ የኦነጋዊያንን አካሄድ አውግዘዋል።
Source: Link to the Post