በኮሚሽነር አበረ አዳሙ ድንገተኛ ሕልፈት የተሰማውን ሀዘን የገለፀው ዓለም አቀፍ የዐማራ ኅብረት(ዓየኅ) የአስከሬን ፎረንሲክ ምርመራ ተጣርቶ ለቤተሰባቸው፣ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለህዝብ ይፋ እን…

በኮሚሽነር አበረ አዳሙ ድንገተኛ ሕልፈት የተሰማውን ሀዘን የገለፀው ዓለም አቀፍ የዐማራ ኅብረት(ዓየኅ) የአስከሬን ፎረንሲክ ምርመራ ተጣርቶ ለቤተሰባቸው፣ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለህዝብ ይፋ እን…

በኮሚሽነር አበረ አዳሙ ድንገተኛ ሕልፈት የተሰማውን ሀዘን የገለፀው ዓለም አቀፍ የዐማራ ኅብረት(ዓየኅ) የአስከሬን ፎረንሲክ ምርመራ ተጣርቶ ለቤተሰባቸው፣ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለህዝብ ይፋ እንዲደረግ አሳሰበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከቅርብ ቀናት በፊት ከስልጣን የተነሱት የዐማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት ኮሚሽነር አበረ አዳሙ በድንገተኛ የልብ ህመም ምክንያት ወደ ሆስፒታል የሄዱ ቢሆንም ኮሚሽነሩ በሕይወት መትረፍ አለመቻላቸውን የክልሉ ኮሚንኬሽን ቢሮ ዘግቧል። ኮሚሽነሩ የተሰማቸውን ድንገተኛ ስሜት መሠረት አድርገው ባህርዳር ቀበሌ 14 ድሪም ኬር ጠቅላላ ሆስፒታል በጠዋቱ የሄዱ ቢሆንም ህመማቸው በድሪም ኬር መፍትሔ እንደማያገኝና ወደ ተሻለ ህክምና ባህርዳር ከተማ ሰባታሚት ወደ ሚገኘው ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሪፈር ቢባሉም ህመማቸው ሊታገስና በህይወት ሊተርፉ አልቻሉም ብሏል ኢፕድ። በመሆኑም የኮሚሽነሩ ሞት ድንገተኛና አሳዛኝ መሆኑን የተረዳው ማህበራችን የእኒህ ኮሚሽነር አስከሬን ፎረንሲክ ምርመራ ተጣርቶ ለቤተሰባቸው ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ምንም ይሁን ምንም ወክለው ለዓመታት ላገለገሉትና ለተገኙበት ማህበረሰብና ህዝብ የክልሉ መንግስት ውጤቱን ያስረዳ ዘንድ ዓለም አቀፍ የዐማራ ኅብረት ጠይቋል። በመጨረሻም ከክልሉ ውጭ ወደ ክልሉ ውስጥ ገብቶ ከዚያም አልፎ እርስ በርሳችንን ለማነታረክ ይሔው ብዙ ሴራዎች በህዝባችን ላይ እየተሸረበና እየተጎነጎነ በመሆኑ የክልላችን ሕዝብ በተለይ ወጣቱ የተለያዩና የተጣረሱ ሀሳቦችን ከመሠንዘር እንዲቆጠብ ማህበሩ አሳስቧል። ከዛሬው በመነሳት የነገውን መፍትሔ እንድናስቀምጥና ሰው በሰውነቱ ብቻ በድንገተኛ መንገድ የተፈጥሮም ይሁን ሰው ሰራሽ አደጋና የህይወት ማጣት ሲገጥመው በሕይወት ካጣነው ጀርባ ያሉትን ንጹሀንን በማሰብ ወቅታዊና ብስለት የሌላቸው ትርጓሚያቸው አሻሚና አወዛጋቢ ለጠላት ምቹ የሆኑ ጽሁፎችን ባለመፃፍ ትቆጠቡ ዘንድ ዓለም አቀፍ የዐማራ ኅብረት በጽኑ ያሳስባል ነው ያለው። ምንም ቢሆን የጠላቴ ጠላት የኔም ወዳጀ ነው የሚለውን መርህ የአማራ ሕዝብ የሚጠቀምበት የአባቶቹ ብስለት የተሞላበት መርህ የምንጠቀመው አሁን ነውና በስክነትና በብስለት እንድንመራ ማሳሰብ እንወዳለን ብሏል ማህበሩ በመግለጫው። በመጨረሻም ዓለም አቀፉ የአማራ ሕብረት ለኮሚሽነሩ ቤተሰቦች ወዳጅ ጓደኞቹና ለመላው የዐማራ ህዝብ መጽናናትን እንመኛለን ብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply