በኮሜዲያን እሸቱ መለሰ አስተባባሪነት ከ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች በችግር ምክኒያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ተደረገ። ባህርዳር:- ሚያዚያ…

በኮሜዲያን እሸቱ መለሰ አስተባባሪነት ከ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች በችግር ምክኒያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ተደረገ። ባህርዳር:- ሚያዚያ 18/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ እንደገለፀው የድጋፉ መነሻ ከአባታችን አቡነ በርናባስ ጥሪ ተደርጎልን ሰቆጣ መጥተን የተፈናቀሉ ወገኖችን ያሉበትን ችግር ካዬን በኋላ የአባታችን መልእክት በማስተላለፍ ለህዝብ ባቀረብነው የድጋፍ ጥሪ መሰረት የተገኘ ድጋፍ መሆኑን ገልፀዋል። የመጣው ደጋፍም ከግለሰቦችና ድርጅቶች የተገኙ ዱቄት፣ ዘይት፣ብርድ ልብሶች፣ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች፣ አልባሳት እና ሌሎችን ጨምሮ መሆኑን የገለፁት ኮሜዲያን እሸቱ መሰለ በአጭር ቀናት ውስጥ ድጋፉ ለተጠቃሚዎች እንዲደርስ የትራንስፖርት እና ሌሎች ወጭዎችን በማመቻቸት ለዚህ ሰርጭት ላደረሰልን ለዋግ ልማት ማህበር ሊያስመሰግን የሚችል ስራ ነውና በርቱልን በማለት ምስጋና አቅርበዋል። የዋግ ልማት ማህበር ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አምላኩ አበበ በበኩላቸው የልማት ማህበሩ በተፈጠረው ችግር መክንያት በርካታ ድጋፎችን በማሰባሰብ እና ድጋፍ ለሚያደርጉ ግለሰቦች መረጃ በመስጠት የተፈናቃይ ወገኖችን ችግር ለመቅረፍ ጥረት እያደረገ ያለ የህዝብ ማህበር መሆኑን ገልጸዋል ። አቶ አምላኩ አበበ አያይዘው እንደገለፁት ኮሜድያን እሸቱ መሰለ በአካባቢያችን ያለዉን መሠረታዊ ችግር በተገቢው መንገድ ከተረዱ በኋላ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን ለመርዳት ባደረጉት ጥረት 136 ኩ/ል ዱቄት ፣ 740 ሊትር ዘይት ፣ 200 ብርድ ልብስ ፣ 267 የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ፣ 40 ኩ/ል አልባሳት እና ሌሎችን ጨምሮ ያመጡትን 2 ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ ተረክበን ባሉበት ለተጠቃሚዎች አሰራጭተናል ብለዋል ። ከሁሉም በላይ ግን ይላሉ አቶ አምላኩ አበበ የአካባቢያችን መሰረታዊ ችግር በሚዲያ አዉጥተዉ ፣ ሚዲያቸዉን ተጠቅመው ፣ ድጋፍ አሰባስበው እና በአካል እዚህ ተገኝተው ድጋፉን ለእናቶችና ህፃናት ፣ ለአካል ጉዳተኞችና ለአረጋውያን ባሉበት ማሰራጨት መቻሉ ኮሜዲያን እሸቱ ያከናወነው ተግባር የህዝብ ወገንተኝነት ያሳየበት ትልቅ ስራ መሆኑን ገልጸው ድጋፉን ላደረጉ ወገኖች በሙሉ በዋግ ልማት ማህበር እና በተፈናቃይ ወገኖች ስም ምስጋና አቅርበዋል ። በዓለም ዙሪያ ያላችሁ ወገኖች በክርስቶስ ትንሳኤ የምታምኑ እና የእምነቱ ተከታይ ለሆናችሁ በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ ። ይህ በዓል ትልቅ በዓል ሲሆን ለእምነቱ ተከታዬች የነፃነት ፣የሰላም ፣የፍቅር እና የደስታ በዓል መሆኑን የዋግ ኽምራ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ በርናባስ ገልፀዋል። የተደረገውን ጥሪ ሰምታችሁ ወገናችሁን ለመደገፍ ያደረጋችሁት ተሳትፎ ርህራሄና አንድነታችሁን የሚገልፅ በመሆኑ በእውነቱ ለሚዲያው አካላትና ድጋፍ ላደረጉ ወገኖች በአንድነት ልትመሰገኑ ይገባልም ብለዋል አበታችን አብነ በርናባስ። አባታችን አቡነ በርናባስ አክለው እንደገለጹት ኮሜዲያን እሸቱ መሰለ በከተማችን ያለዉን ችግር አይቶና ተረድቶ በችግር ውሰጥ ያለውን ህዝብ ለማገዝ አቅሙ በፈቀደው መጠን ባደረገው እንቅስቃሴ ምግብ ነክና ሌሎች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አሰባሰቦ ያመጣቸውን ንብረቶች ተረክበናል ለተረጅዎችም በቀጥታ አሰራጭተናል በመሆኑም ላደረጋችሁት በጎ ስራ አግዛብሔር ለሁላቹሁም ዋጋችሁን ይክፈላችሁ ብለዋል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply