በኮምቦልቻ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የ2013 የኢትዮጵያ ውሃ ዋና ሻምፒዮና ውድድር ተጠናቀቀ

በኮምቦልቻ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የ2013 የኢትዮጵያ ውሃ ዋና ሻምፒዮና ውድድር ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ ለ7 ቀናት ሲካሄድ የቆየው ዓመታዊው የኢትዮጵያ ክልሎችና ክለቦች ውሃ ዋና ሻምፒዮና ውድድር በአማራ ክልል አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ሻምፒዮናው በደማቅ ሁኔታ ሲጠናቀቅ በመጨረሻው ቀን አምስት የፍጻሜ ውድድሮች ተካሂደዋል፡፡

በውድድሩ የአማራ ክልል በወንድ፣በሴት እና በታዳጊ ምርጥ ስፖርተኛ ዘርፍ ዋንጫ የወሰደ ሲሆን፣ ክልሉ አጠቃላይ አሸናፊ መሆንም ችሏል፡፡

አዲስ አበባ  በስፖርታዊ ጨዋነት ዋንጫ ያገኘ ሲሆን÷የኦሮሚያ ፖሊስ ደግሞ ለውሃ ዋና ስፖርት እድገት ላበረከተው አስተዋጽኦ የውድድሩ ልዩ ተሸላሚ መሆን ችሏል፡፡

በተጨማሪም ለሻምፒዮናው ምርጥ አሰልጣኝ እና እንደ አጠቃላይ ለውሃ ዋና ስፖርት እድገት አስተዋጽኦ ላደረጉ ሁሉ ልዩ የምስጋና ሽልማት ተበርክቷል፡፡

በሌላ በኩል በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር እና በኢትዮጵያ ውሃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን በጋራ ለሚገነባው የመዋኛ ገንዳ የይዞታ ማረጋገጫ  ስኬች ርክክብ  መደረጉን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በኮምቦልቻ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የ2013 የኢትዮጵያ ውሃ ዋና ሻምፒዮና ውድድር ተጠናቀቀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply