በኮሬ ብሄር ተወላጆች ላይ በታጣቂዎች እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል የፌዴራል መንግሥት በፍጥነት ጣልቃ በመግባት እንዲያስቆም የአማሮ ወረዳ ነዋሪዎች ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል…

በኮሬ ብሄር ተወላጆች ላይ በታጣቂዎች እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል የፌዴራል መንግሥት በፍጥነት ጣልቃ በመግባት እንዲያስቆም የአማሮ ወረዳ ነዋሪዎች ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 4 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በትናንትናው እለት በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ጎልቤ በተባለ ቀበሌ፣ የም/ጉማጅ ዞን የጋላና ወረዳ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት በሦስት ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ ስለመድረሱ የአማሮ ወረዳ ነዋሪዎች ገልፀዋል። ሚያዚያ 03_08_2013 የአማሮ ወረዳ የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት እንደገለፀው በአማሮ ወረዳ ጎልቤ ቀበሌ፣ የም/ጉማጅ ዞን የጋላና ወረዳ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት በሦስት ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ ደርሷል። ጥቃት አድራሾቹ ከጋላና ወረዳ ጅርምና መሰል በተባሉት ቀበሌዎች መሽገው የነበሩ የታጠቁት ሀይሎች ወደ አማሮ ወረዳ ቀበሌዎች ዘልቀው በመግባት ነው በጎልቤ ቀበሌ ነዋሪዎች ላይ ጉዳት ያደረሱት። የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሁለት ሰዎች ከጎልቤ ቀበሌ፣ አንድ ደግሞ ከአጎራባች ቀበሌ መሆኑን ጥቃቱ የደረሰባቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። አካባቢውን ለማረጋጋት የፌዴራል ፖሊስም ሆነ ሌሎች የጸጥታ አካላት ጥረት እያደረጉ ቢሆንም ሰላም ማምጣት አለመቻሉን የአካባቢ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። ሚያዚያ 1_2013 የአንድ ሠው ህይወት ከማለፉ በተጨማሪ 140 ከብቶች መዘረፋቸውን አስተያየት ሰጪዎች ገልጸዋል። ይህን ተከትሎ ነው መንግሥት በፍጥነት ገብቶ ከኮሬ ህዝብ ጫንቃ ላይ በጸረ ሠላም ሀይሎች እየደረሰ ያለውን ጥቃት እንዲያስቆም የከሬዳ፣ የጃሎ፣ የዳኖ፣ የቆሬ፣ የጎልቤ፣ የዬሮና መሠል ቀበሌ ነዋሪዎች የጠየቁት ሲል የአማሮ ወረዳ የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ዘግቧል። በጽንፈኛ ሀይሎች የተቀናጀ የዘር ማጥፋት ዘመቻ በኮሬ ህዝብ ላይ ተጠናክሮ መቀጠሉን የገለፁት ነዋሪዎች እየደረሰ ላለው ጥቃት የፈረሰውን የሰገን ዞንን ወደ ጎማይዴ ልዩ ወረዳ እንቀይራለን የሚሉ ጽንፈኞችና በነጭ ሣር ፓርክ በህገ ወጥ መንገድ የመሸጉ የጉጅ ታጣቂዎችን ተጠያቂ አድርገዋል። በኮሬ ማህበረሰብ ላይ በጉጂ ታጣቂዎች ከደረሱ ወርሃዊ የዘር ማጥፋት ዘመቻዎች መካከል በሚል የኮሬ ድምፅ የሆኑት ሚድያዎች KWT_KWD editorial teams ኦን ላይን ሚድያዎች ያደረጉት የዳሰሳ ሪፖርት እንዳመለከተው:_ 1. በቀን 8-7-2013 ዓ.ም አርሶአደር ኤርምያስ ኤባላ ሻሮ ቀበሌ በጉጂ ታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት የቆሰለ። 2. በቀን 8-7-2013 ዓ.ም አርሶአደር አለሙ ጭርቆስ ሻሮ ቀበሌ ሕይወቱ አልፏል። 3. በቀን 9-7-2013 ዓ.ም ወጣት አስረስ አሻግሬ ከሬዳ ቀበሌ ሕይወቱ አልፏል። 4. በቀን 8-7-2013 ዓ.ም አርሶአደር መሠለ ገነነ አልፍጮ ቀበሌ ሕይወቱ አልፏል። 5.በቀን 20-7-2013 ዓ.ም አርሶአደር አዱኛ ሉቃስ ቆሬ ቀበሌ ሕይወቱ አልፏል። 6. በቀን 20-7-2013 ዓ.ም አርሶአደር ኢሳ ሹሌ ቆሬ ቀበሌ ሕይወቱ አልፏል። 7. በቀን 21-7-2013 ዓ.ም ከጃሎ ቀበሌ አ/አደር አገኘው ሲሳይ በዘግናኝ አገዳደል ሕይወቱ አልፏል፡፡ 8. በቀን 22-7-2013 ዓ.ም አርሶአደር ዮሐንስ ባሀረን ጋሙሌ ቀበሌ እቤታቸው ተኝተው እያሉ በመግባት ሕይወቱ አልፏል። 9. በቀን 23-7-2013 ዓ.ም ወጣት አንበሰ ኩሩዋዴ ከሬዳ ቀበሌ ሕይወቱ አልፏል። 10.በቀን 25-7-2013 ዓ.ም አርሶአደር ቦልሳኤ ቦክያዴ ደርባ ቀበሌ ልዩ ቦታ ትንሹዋ ነጭሳር ሕይወቱ አልፏል። 11. በቀን 25-7-2013 ዓ.ም ወጣት ሚል (ሚልሻ) ባልቻ ደርባ ቀበሌ የቆሰለ። 12.በቀን 24-26-7-2013 ከፍተኛ ውጊያ በአምስት ቀበሌዎች ተካሂዷል ከከሬዳ እስከ ቆሬ ቀበሌ። በዚህም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ነዋሪዎች ከዶርባዴ እና ጃሎ ቀበሌ የተፈናቀሉ ሲሆን 6394 አባወራና እማወራ ተፈናቅለዋል። 13. በቀን 24-25-2013 ዓ.ም በጉጂ ታጣቂዎች ከፍተኛ ውጊያ በቡኒት ፣አቡሎና አልፋጮ ቀበሌዎች ላይ የተካሄደ ሲሆን በዛው ዕለት በትንሿ ነጭ ሳር ስምንት በረት ሙሉ የነበረ ከ460 በላይ ከብቶች ተዘርፈዋል። 14. በቀን 28-7-2013 ዓ.ም ከምዕራብ ጉጂ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች የወረራ ጦርነት ከፍተው ዶርባዴ ፣ ከሬዳና ጃሎ ቀበሌዎች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል። 15. በቀን 01-8-2013 ዓ.ም ቆሬ ቢቆ ቀበሌ የምዕራብ ጉጂ ታጣቂዎች የወረራ ጦርነት ከፍተው አርሶአደር ኡካያ ኡሳታ ሕይወቱ አልፏል፣ 140 በላይ ከብቶች ተዘርፈዋል፣ በቀኑም በሌሎች ቀበሌዎች ላይ ከፍተኛ ተኩስ ተከፍተው ነበር። 16. በቀን 02-8-2013 ዓ.ም በጎልቤ-ዳኖ-ቆሬ ቢቆ ቀበሌዎች ላይ የምዕራብ ጉጂ ታጣቂዎች የወረራ ጦርነት ከፍተው ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል። 17. አሁንም ከሌሊት ጀምሮ ጎልቤ ቀበሌ ላይ የምዕራብ ጉጂ ታጣቂዎች የወረራ ጦርነት ከፍተዋል። በዚህም ሁለት አርሶአደሮች ቆስለዋል። የሟቾቹ ቁጥር ከዚህ ሊበልጥ እንደሚችልም ተመላክቷል። ስለሆነም የኢትዮጵያ መንግሥት በኮሬ ብሔር ላይ የተከፈተውን የዘር ማጥፋት ጦርነት እንዲያስቆም የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ሚዲያ፣ ፖለቲካዊ ፓርቲዎች፣ አገራዊ እና ዓለማቀፋዊ ሰብዓዊ ድርጀቶች ግፊት እንዲያደርጉ ጥሪም ቀርቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply