በኮቪድ-19 ወረርሺኝ ተስተጓጉለው የነበሩ የቅርስ ጥገናዎችን ለማስቀጠል እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

በኮቪድ-19 ወረርሺኝ ምክንያት የጥገና ስራው ተቋርጦ የነበረውን የአክሱም ሃውልት እድሳቱን ለማስቀጠል እቅድ መያዙን የኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን  ጠቁሟል፡፡

በተመሳሳይ የላሊባላ ውቅር አቢያተ ክርስቲያናትን ጥገና ለማስቀጠል መጠለያ ድንኳኖች እንዲነሱ የተወሰነ ሲሆን በዚህ መሠረት ቅርሱ በማይጎዳ መንገድ ድንኳኖቹ እንዴት መነሳት እንዳለባቸው በተለያዩ ኮሚቴዎች ተጠንቷል ተብሏል፡፡

ጥናቱም ለዩኔስኮ እንደተላከ የኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ነዳች ጀማል ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡የጢያ ትክል ድንጋይ የቅርስ ጥገናም ባለሙያዎቹ በቦታው ተገኝተው ስራቸውን እያከናወኑ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

**********************************************************************

ዘጋቢ አብርሃም አያሌው

ቀን 22/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply