በኮንስትራክሽን ዘርፉ ያለው የጨረታ ሂደት የሃገር ውስጥ ኮንትራክተሮችን የሚያገል ነው ተባለየሀገሪቱን ፕሮጀክቶችን ለመገንባት የሚወጡ ጨረታዎች ብዙውን ጊዜ የሀገር ውስጥ ተቋራጮችን የሚያ…

በኮንስትራክሽን ዘርፉ ያለው የጨረታ ሂደት የሃገር ውስጥ ኮንትራክተሮችን የሚያገል ነው ተባለ

የሀገሪቱን ፕሮጀክቶችን ለመገንባት የሚወጡ ጨረታዎች ብዙውን ጊዜ የሀገር ውስጥ ተቋራጮችን የሚያገል እና ሀገሪቱ ያለችበትን ሁኔታ ያላገናዘበ እንደሆነ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ተቋራጭ ማህበር ገልጿል።

የማህበሩ የቦርዶ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አለማየው ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ጨረታው ትልቅ አቅም ላይ ነን ለሚሉ ተቋራጮች እንኳን የሚከብድ እንዲሁም የውጪ ተቋራጮችን ብቻ ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል።

የቦርዱ ሰብሰባ ለጨረታው የሚወጣው መስፈርት እና የሚስራው ስራ በጥናት ያልተጠና ሁልጊዜ ተመሳሳይ ጨረታዎች በስራ ላይ እንደሚውሉም አንስተዋል።

በተለይም አሁን ላይ ሃገሪቷ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች አብዛኛው በሚባል ሁኔታ በውጭ ተቋራጮች መያዛቸውን ሃላፊው ተናግረዋል፡፡

ምክንያቱ ደግም የሃገር ውስጥ ተቋራጮችን ታሳቢ ያደረገ የጨረታ ችግር እንዲሁም ለሃገር ውስጥ ተቋራጮች የሚሰጠው ግምት አናሳ በመሆኑ ነዉ ብለዋል

ለአለም አሰፋ
መጋቢት 19 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply