በኮንሶ እና በአሌ አከባቢ ተፈጥሮ የነበረውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት ውይይት እየተካሄደ ነው

በኮንሶ እና በአሌ አከባቢ ተፈጥሮ የነበረውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኮንሶ እና በሌ አከባቢ ተፈጥሮ የነበረውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
በውይይቱ የኮንሶ እና የሌ ህዝቦች ለረጅም ዘመናት የዘለቀ አብሮነታቸውን በማስቀጠል እርስ በርስ እንደ አንድ የቤተሰብ አባል ሆነው መዝለቃቸው ተነስቷል፡፡
ይህ አንድነታቸው ያላስደሰታቸው አካላት ግን የግል ጥቅም እና ፍላጎታቸውን መሠረት በማድረግ የጸጥታ ችግር እንዲከሰት ምክንያት ሆነዋል ነው የተባለው፡፡
ዛሬ ግን የኮንሶ እና የኸሌ ህዝቦች የቀደመ ሠላማቸውን ለማስቀጠል በየአካባቢያቸው ያለውን የመተሳሰብ እና የመደጋገፍ ባህል ለማስቀጠል ውይይት በማካሄድ ላይ ናቸው፡፡
በመድረኩ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው፣ የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጥላሁን ከበደን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች መገኘታቸውን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በኮንሶ እና በአሌ አከባቢ ተፈጥሮ የነበረውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት ውይይት እየተካሄደ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply