በኮንጎ የጣሊያን አምባሳደር ተገደሉ

https://gdb.voanews.com/43F1D5BD-31C0-4D16-A435-1FC7912F213F_cx0_cy11_cw0_w800_h450.jpg

በዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፖብሊክ የጣሊያን አምባሳደር ምስራቅ ኮንጎ ጉዞ ላይ እንዳሉ በአጥቂዎች መገደላቸው ተነገረ።

የጣሊያን ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ አምባሳደር ሉካ አናስታዚያ ከተባበሩት መንግሥታት የድርጅት የኮንጎ አረጋጊ ተልዕኮ ጋር በአጀብ በመጓዝ ላይ ሳሉ በምሥራቅ ኮንጎዋ ጎማ ከተማ አቅራቢያ ባደፈጡ አጥቂዎች እንደተገደሉ አመልክቷል። አብሩዋቸው የነበረ ጠባቂ ወታደርም ተገድሏል።

ሮይተርስ የቪሩንጋ ብሄራዊ ፓርክን ጠቅሶ ሲዘግብ አምባሳደሩ የተገደሉት በጥበቃ አጀብ ይጉዋዙ በነበሩት መኪናዎች ላይ ጠለፋ ለመፈጸም በሞከሩ አጥቂዎች እንደሆነ ገልጿል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply