በወለጋ አሙሩ ወረዳ የሚኖሩ አማራዎች መረጃ ለሚዲያ አካላት ታደርሳላችሁ በሚል ምክንያት ከፍተኛ ችግር እየደረሰባቸው እንደሆነ  የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡…

በወለጋ አሙሩ ወረዳ የሚኖሩ አማራዎች መረጃ ለሚዲያ አካላት ታደርሳላችሁ በሚል ምክንያት ከፍተኛ ችግር እየደረሰባቸው እንደሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡…

በወለጋ አሙሩ ወረዳ የሚኖሩ አማራዎች መረጃ ለሚዲያ አካላት ታደርሳላችሁ በሚል ምክንያት ከፍተኛ ችግር እየደረሰባቸው እንደሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ፡-18/04/13/ዓ.ም ባህር ዳር በወለጋ አሙሩ ወረዳ የሚኖሩ አማራዎች ዛሬም እየተፈናቀሉ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ የሚፈናቀሉት ደግሞ በማንነታቸው ምክንያት እንደሆና ለሚዲያ አካላት መረጃ ታደርሳላችሁ በሚል ጭምር እንደሆነም ተፈናቃዮች ተናግረዋል፡፡ ከወለጋ አሙሩ ወረዳ በምንኖር የአማራ ተወላጆች ላይ ብዙ ግፍና በደል እየደረሰብን ይገኛል ሲሉ ነዋሪዎች ለአሻራ ሚዲያ ገልጸዋል፡፡ በወረዳው ለተፈጠረውና እየተደረገ ላለው የዘር ማጥፋትና የማፈናቀል ወንጀል ከቀበሌ እስከ ወረዳ ያሉ ከፍተኛ የስራ አመራሮች ለአጥፊው ቡድን ተባባሪ እንደሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም በወለጋ ለሚካሄደው የዘር ጭፍጨፋና ማፈናቀል እንዲሁም እንግልት ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች ግንባር ቀደም ተዋኒያን በመሆናቸው መንግስት ለህግ ማቅረብና ተጠያቂ ማድረግ እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም በወለጋ የሚደረገውን ዘርን የማጥፋት ጥቃትና አጥፊዎችን መንግስት በችልተኝነት መመልከቱን ምንጫችን ኮንነዋል፡፡ ችግሩ በተፈጠረበት አካባቢ የሚኖሩ ንጹሀን ዜጎች ለሚመለከተው አካል ብናመለክትም እስካሁን ግን የደረሰልን የመንግስት አካል የለም የኦነግ ታጣቂዎችም ቤት እያቃጠሉ ንብረት እየዘረፉ ነው ሲሉ ምንጫችን ለአሻራ ሚዲያ ገልጸዋል፡፡ ስለሆነም መንግስት ተጨማሪ የመከላከያ ሰራዊት አሁኑኑ አከባቢው ላይ እንዲገባ ማድረግ እንዳለበትና የዜጎችን ህይወት ማትረፍ እንዳለበት የአካባቢው ነዋሪዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply