You are currently viewing በወለጋ አማራዎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን የተቀናጀ ጥቃት በማውገዝ ለኢሰመጉ መረጃ ሰጥተው፣ ትኩረት እንዲደረግ አሳስበው ወደቤታቸው ሲመለሱ በልደታ ፖሊስ የታሰሩ የአካባቢው ተወላጆች ከእስር…

በወለጋ አማራዎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን የተቀናጀ ጥቃት በማውገዝ ለኢሰመጉ መረጃ ሰጥተው፣ ትኩረት እንዲደረግ አሳስበው ወደቤታቸው ሲመለሱ በልደታ ፖሊስ የታሰሩ የአካባቢው ተወላጆች ከእስር…

በወለጋ አማራዎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን የተቀናጀ ጥቃት በማውገዝ ለኢሰመጉ መረጃ ሰጥተው፣ ትኩረት እንዲደረግ አሳስበው ወደቤታቸው ሲመለሱ በልደታ ፖሊስ የታሰሩ የአካባቢው ተወላጆች ከእስር ተለቀዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 28 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በአዲስ አበባ ልደታ አካባቢ ወደ በኢሰመጉ ቢሮ አቅንተው በወለጋ በመንግስት የጸጥታ አካላት ጭምር በአማራዎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግድያ፣መፈናቀል እና መሳደድን በማውገዝ መረጃ የሰጡና ትኩረት እንዲያደርግ አሳስበው ከቢሮ ሲወጡ የታሰሩ 22 የአካባቢው ተወላጆች እንደነበሩ አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) መዘገቡ ይታወቃል። በተለይም ህዳር 24/2015 በአንገር ጉትን እና አንዶዴ ዲቾ በተመሳሳይ እለት የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና ከሌሎች አጋሮቻቸው ጋር በመቀናጀት በአማራዎች ላይ ይፋዊ ጦርነት በመክፈት በርካቶችን መግደላቸው፣ ማቁሰላቸውና ማፈናቀላቸውን ተከትሎ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) መረጃ በመስጠት በትኩረት እንዲከታተለው አሳስበው ነበር። በልደታ ከቢሮ በር ሲወጡም በፖሊስ ተይዘው በተክለ ሀይማኖት አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ከህዳር 24/2015 ጀምሮ ያልተፈቀደ ሰላማዊ ሰልፍ በሚል የፖሊስ ውንጀላ ላለፉት 4 ቀናት በእስር ላይ ቆይተዋል። ህዳር 27/2015 በልደታ ተክለ ሀይማኖት አካባቢ ፍ/ቤት ቀርበው እያንዳንዳቸው በ500 ብር ዋስትና ከእስር የተፈቱ መሆናቸውን አሚማ ለማወቅ ተችሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply