በወለጋ እና በመተከል ለኦነግ እና ለጉምዝ ጦር የፋይናስ ፣ የነዳጅ እና የትጥቅ አጠቃላይ የሎጀስቲክስ ምንጩ የኦነግ ጭንብሉ የኦሮሞ ብልፅግና ነው። (ታህሳስ፡-24/04/13/ዓ.ም…

በወለጋ እና በመተከል ለኦነግ እና ለጉምዝ ጦር የፋይናስ ፣ የነዳጅ እና የትጥቅ አጠቃላይ የሎጀስቲክስ ምንጩ የኦነግ ጭንብሉ የኦሮሞ ብልፅግና ነው። (ታህሳስ፡-24/04/13/ዓ.ም ) በመተከል ና በወለጋ የሃይል አሰላለፉን በጠላት ሚዛን እንዲደፉ ያደረገው የሎጀስቲክስ ስምሪቱ እና የዘመቻ ማመጣጠን ስራው በመንግስት ስም ባሉት የኦሮሞ ብልፅግና ሰዎች እየተሰራ ስለሆነ ነው ሲሉ ምንጮች አመላክተዋል፡፡ የኦነግ ጦር እስካሁን ባደረጋቸው ዘግናኝ ግድያወች ውስጥ በተለይ በጥይት የፈፀማቸው ሲፈተሹ በኢትዩጲያ ህዝብ ሀብት በውጭ ምንዛሬ የተገዙ እና በኦሮሞ ብልፅግና ውስጥ ባሉ የመሳሪያ ዲፓዎች በስራ ሀላፊዎች ትዕዛዝ እየተዛቁ የተሰጡት ስለመሆናቸውም ምንጮች ለአሻራ ሚዲያ ገልጸዋል። በሀገር ውስጥ በመከላከያ ኢንጂነሪግ የተገጣጠሙ ባለ ሌንስ ክላሽንኮብ ጨምሮ በቅርቡ ከ1 አመት በፊት ጀምሮ እስካሁን በተለያየ ዙር ወደ ሀገር ውስጥ የገቡት እንደ ስናይፕር ዓይነት የአንዱ ዋጋ ቢያንስ ከግማሽ ሚሊየን ያላነሰ የኢትዩጲያ ብር ወጭ የሆነበት በውጭ ምንዛሬ የተገዛ ጨምሮ አዳዲስ ዘመኑን የዋጁ ክላሾች ኦነግ ጦር እንደ ኦሮሚያ ልዩ ሃይል እንዲታጠቅ መደረጉም ተጠቁሟል። በኢትዩጲያ ህዝብ ጥሪት እየተገዙ ገዳዮች የታጠቁት መሳሪዎች ልክ እንደህወሓት ዘመኑ አልሸባብን የማስታጠቁ ተግባር ከተረኝነት አዘቅት በተጠናወታቸው የኦነግ የዘመኑ ቁንጮዎች ኦነግን በሀገር ውስጥ እስከ ኬንያ ለማስታጠቅ እና የእርዳታ አይን ለመሳብ እስከሚደርስ ፕሮጀክት ኦሮሙማን እውን ለማድረግና የበላይ ለመሆን የኦሮሞ ብልጽግና እየሰራ መሆኑንም ምንጫችን ገልጸዋል። ይሁን እንጅ ይህ አስተሳሰብ መቼም አይሳካለቸውም ይልቁንም በዚህ አካሄዳቸው የሚቀጥሉ ከሆነ የአባታቸው ህውሀት እጣ ፋንታ ይገጥማቸዋል ሲሉ ምንጫችን ተናግረዋል፡፡ ይህ አካሄዳቸው ደግሞ ከጅምሩ እየከሸፈባቸውና በስልጣን ሽኩቻ እርስ በርስ እስከመበላላት እየደረሱ ያለበት ሁኔታ መስተዋሉንም አንስተዋል። በዚህ አካሄዳቸው ህዝባዊ ቁጣው ህዝባዊ ትግል እየወለደ ይገኛል። ስለሆነም ከትናንት ያልተማሩ ተረኞችን ሀቀኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ዳግም ያስወግዳል ሲሉ ምንጫችን መልዕክት አስተላልፈዋል። ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ https://m.youtube.com/channel/UCsfBw4xrhJzdMTzhWk_uX2A…

Source: Link to the Post

Leave a Reply