በወለጋ ከተፈፀመባቸው ጥቃት ሸሽተው ወደ አዲስ አበባ ገብተው የነበሩ እና ወደ አርሲ እንዲመለሱ የተደረጉ ከ300 በላይ ተፈናቃዮች ዛሬም ማረፊያ አለማግኘታቸው ተገለጸ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል…

በወለጋ ከተፈፀመባቸው ጥቃት ሸሽተው ወደ አዲስ አበባ ገብተው የነበሩ እና ወደ አርሲ እንዲመለሱ የተደረጉ ከ300 በላይ ተፈናቃዮች ዛሬም ማረፊያ አለማግኘታቸው ተገለጸ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 16 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በወለጋ ከተፈፀመባቸው ጥቃት ሸሽተው ወደ አዲስ አበባ ገብተው የነበሩ እና ወደ አርሲ ዞን አቦምሳ ወረዳ እንዲመለሱ የተደረጉ ከ300 በላይ ተፈናቃዮች ዛሬም ማረፊያ አላገኙም፡፡ የአዲስ አበባ መስተዳድር ወደ ደብረ ብርሃን እና ቀጥሎ ወደ አርሲ ቢልካቸውም በሁለቱም ሥፍራ እጁን ዘርግቶ የሚቀበላቸው ወገን አጥተዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም አቦምሳ ከተማ ላይ ካጓጓዛቸው መኪና ጋር እንዳይንቀሳቀሱ ታግደው እንደሚገኙ ነግረውናል ሲል ሸገር ኤፍ ኤም ራዲዮ ዘግቧል፡፡ ፎቶ_አርሲ አቦምሳ By Sintayehu Chekol

Source: Link to the Post

Leave a Reply