You are currently viewing በወለጋ ከአሳዛኙ የቶሌ የጅምላ ጭፍጨፋ ተርፈው ወደ ወሎ ሲጓዙ የነበሩ ከ90 በላይ አማራዎች አዲስ አበባ ከመግባታቸው ተገደው እንዲመለሱ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ሰኔ 30 ቀ…

በወለጋ ከአሳዛኙ የቶሌ የጅምላ ጭፍጨፋ ተርፈው ወደ ወሎ ሲጓዙ የነበሩ ከ90 በላይ አማራዎች አዲስ አበባ ከመግባታቸው ተገደው እንዲመለሱ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሰኔ 30 ቀ…

በወለጋ ከአሳዛኙ የቶሌ የጅምላ ጭፍጨፋ ተርፈው ወደ ወሎ ሲጓዙ የነበሩ ከ90 በላይ አማራዎች አዲስ አበባ ከመግባታቸው ተገደው እንዲመለሱ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በወለጋ ከአሳዛኙ የቶሌ የጅምላ ጭፍጨፋ ተርፈው ወደ ወሎ ሲጓዙ የነበሩ ከ90 በላይ አማራዎች አዲስ አበባ ከመግባታቸው ተገደው እንዲመለሱ መደረጉን ተሳፋሪዎች ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ተናግረዋል። ከሰኔ 11/2014 ዘር ተኮር ጭፍጨፋ የተረፉ ከ90 በላይ ሆነው በህዝብ ማመላለሻ መኪና ወደ አዲስ አበባ የመጡ አማራዎች መናኽሪያ ከመድረሳቸው ፖሊሶችና ሲቪል የለበሱ አካላት አንዳንዶችን አነጋግረዋል። “እኛ አማራዎች ነን፤ በማንነታችን ከተፈጸመብን ጥቃት ተርፈን፤ ከቀያችን ተፈናቅለን ነው የመጣነው” የሚል ምላሽ ከመስጠታችን ሾፌሩንና ተሳፋሪዎችን አስገድደው በሌሊት ከፊትና ከኋላ በፓትሮል በማጀብ ወደ አምቦ ወስደውናል ብለዋል። ተሳፋሪዎች እንደሚሉት በጊምቢ ወረዳ ከቶሌው ጥቃት ተርፈው በምስራቅ ወለጋ ዞን ዲጋ ወረዳ አርጆ ጉደቱ ከተማ ሰንብተዋል። ሰኔ 29/2014 ከአርጆ ጉደቱ ተነስተው ወደ ወሎ ለማቅናት ከምሽቱ 2 ሰዓት ተኩል አዲስ አበባ ከመድረሳቸው ተገደው እንዲመለሱ ተደርጓል። “አስገድደው መልሰውን አሁን ላይ አምቦ በመከላከያ ካምፕ እንገኛለን” የሚሉት ተሳፋሪዎቹ መልሰው ሲወስዱን መንገድ ላይ ጥቃት ይደርስብናል የሚል ከፍተኛ ስጋት አላቸው። ስለምን በኃይል አስገድደው ይመልሱናል የሚሉት ተሳፋሪዎቹ ለመሆኑ ስለ ህይወታችን ጉዳይ ማን ኃላፊነቱን ይወስዳል ሲሉ ጠይቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply