You are currently viewing በወለጋ የሚፈፀመውን ጭፍጨፋ ለሚድያዎች አጋልጣችኋል በሚል በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች መታሰራቸው ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ታህሳስ 22 ቀን 2015 ዓ/ም…

በወለጋ የሚፈፀመውን ጭፍጨፋ ለሚድያዎች አጋልጣችኋል በሚል በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች መታሰራቸው ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 22 ቀን 2015 ዓ/ም…

በወለጋ የሚፈፀመውን ጭፍጨፋ ለሚድያዎች አጋልጣችኋል በሚል በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች መታሰራቸው ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 22 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በሆሮጉድሩ ወለጋ እና በምስራቅ ወለጋ እየተፈፀመ ስላለው ጭፍጨፋ ለሚድያ ተናግራችኋል በሚል በአዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ስር በሚተዳደሩ አከባቢዎች የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች መታሰራቸውን ቤተሰቦቻቸው ገልፀዋል። በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ እና ሆሮጉድሩ ወለጋ ብቻ በተለይ ከህዳር ወር/2015 ዓ/ም ጀምሮ የክልሉ ልዩ ኃይሎች በከፈቱት ጥቃት 350 የሚደርሱ የአማራ ተወላጆች መገደላቸውን ከአሁን ቀደም መዘገቡን የአማራ ድምጽ አውስቷል። በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ የስራ መስኮች ተሰማርተው የሚኖሩ የወለጋ ተወላጆች በቤተሰቦቻቸው ላይ የተከፈተው ጥቃት እንዲቆም ሚድያዎች፣ የሰብአዊ መብቶች ተቋማት ግፊት እንዲያደርጉላቸው እየጠየቁ ይገኛሉ። በበዚህም በኦሮሚያ ክልል የሚፈፀመውን ጭፍጨፋ በሚዲያ ለምን አጋለጣችሁ በሚል በአዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ስር በሚተዳደሩ አከባቢዎች የሚኖሩ የአማራ ተወላችጆች መታሰራቸውን ነው የታሳሪ ቤተሰቦች አረጋግጠዋል። ለአብነትም በቡራዩ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ከታ አካባቢ ኡመር ክንዴ ተገኘ የተባለ ወጣት ስለ ወለጋው ጭፍጨፋ ለሚድያ ተናግረሀል በሚል ከአስር ቀናት በፊት በክፍለ ከተማው ፖሊሶች በቁጥጥር ስር ውሎ ለእስር የተዳረገ ቢሆንም እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረቡን ቤተሰቦቹ ተናግረዋል። “ወጣት ኡመር ያለ ምንም ፍትህ ከታሰረ ከአስር ቀናት በላይ ሁኖታል፣እስካሁን ፍርድ ቤትም አልቀረበም” የሚሉት ቤተሰቦቹ፡ የኦሮሚያ ክልልን ስም ለማበላሸት ሀሰተኛ መረጃ እየሰጠ ነው በሚል ተጠርጥሮ መታሰሩን ከፖሊስ ጣቢያው አዛዦች መስማታቸውን ገልፀዋል። ከዚህ በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል ስለ ሚፈፀመው ጭፍጨፋ ለሚድያዎች በመናገር የክልሉን ስም እያበላሻችሁ ነው በሚል በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚኖሩ በርካታ የወለጋ ተወላጆች በፖሊስ እየታደኑ መሆኑንም ለማረጋገጥ ተችሏል። የኦሮሚያ ክልል ፀጥታ ኃይሎች በምስራቅ ወለጋ ዞን አንገር ጉቴ ከተማ እና አጎራባች ቀበሌዎች ላይ ከህዳር 24/2015 ዓ/ም ጀምሮ የከፈቱትን ተኩስ የፌደራሉ መንግስት ጣልቃ ገብቶ እንዲያስቆም የሰብአዊ መብቶች ተቋማት ግፊት እንዲያደርጉላችሁ ለመጠየቅ ተሰባስባችኋል በሚል 22 የሚደርሱ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የወለጋ ተወላጆች በአዲስ አበባ ፖሊስ በቁጥጥር ስርውለው ከአራት ቀናት እስር በኋላ እያንዳንዳቸው በ500 ብር ዋስትና ከእስር መፈታታቸው ይታወሳል ሲል የአማራ ድምፅ ሚድያ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply