በወለጋ ጅዳ ወረዳ ድሬ ቀበሌ የኦነግ ወታደሮች ከፍተኛ ጥቃት እየሰነዘሩ እንደሚገኙ ነዋሪዎች ገለጹ በወለጋ ጅዳ ወረዳ ድሬ ቀበሌ የሚገኙ ነዋሪዎች ለአሻራ ሚዲያ በስልክ እንደገለጹት ካለፈው…

በወለጋ ጅዳ ወረዳ ድሬ ቀበሌ የኦነግ ወታደሮች ከፍተኛ ጥቃት እየሰነዘሩ እንደሚገኙ ነዋሪዎች ገለጹ በወለጋ ጅዳ ወረዳ ድሬ ቀበሌ የሚገኙ ነዋሪዎች ለአሻራ ሚዲያ በስልክ እንደገለጹት ካለፈው…

በወለጋ ጅዳ ወረዳ ድሬ ቀበሌ የኦነግ ወታደሮች ከፍተኛ ጥቃት እየሰነዘሩ እንደሚገኙ ነዋሪዎች ገለጹ በወለጋ ጅዳ ወረዳ ድሬ ቀበሌ የሚገኙ ነዋሪዎች ለአሻራ ሚዲያ በስልክ እንደገለጹት ካለፈው አርብ ህዳር 25 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ታህሳስ 01 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ብቻ ከሀያ በላይ የሚሆኑ ንጹሀንን የገደሉ ሲሆን አሁንም በከፍተኛ ሁኔታ ጥቃት እየሰነዘሩ እንደሆነ ገልጸውልናል፡፡ በአካባቢው የኦሮሚያ ልዩ ሀይል የገባ ቢሆንም ሰላሳ የሚሆኑትን የኦሮሚ ልዩ ሀይሎች ታጣቂዎቹ በመግደላቸው ልዩ ሀይሉ ከቦታው ተነስቶ መሄዱን ገልጸው የሟቾች አስክሪን እስካሁን መነሳት አልቻለም ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በቦታው የሚገኙ ምንጫችን ጨምረውም ታጣቂዎቹ ወደ ጅዳ ወረዳ የገቡት በመተከል እንደሆነ እና ከባድ መሳሪያ የታጠቁ ከህወሃት ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያላቸው ስለመሆናቸው ገልጸው አሁን ላይ አካባቢው በከፍተኛ ሁኔታ የተኩስ ድምጽ የሚሰማበት ቦታ ስለሆነ መንግስት ብዛት ያለው ሀይል በአስቸኳይ በመላክ ሊታደገን ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ በወለጋ በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ ንጹሀን ግለሰቦች ብዛት ባላቸውና ዘመናዊ የጦር መሳሪያ በታጠቁ የኦነግ ወታደሮች በየጊዜው ግድያ ሰእና ማፈናቀል እየደረሰባቸው የሚገኙ ሲሆን እስካሁን ቁጣራቸው በውል ያልታወቁት ለህልፈት ሲዳረጉ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ሀብት ንብረታቸው ተቃጥሎ እና ተዘርፎ ለመፈናቀል መዳረጋቸውን አሻራ ሚዲያ በየጊዜው እየተከታተለ ወደ እናንተ ማድረሱ ይታወቃል፡፡ ዘጋቢ፡- ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply