You are currently viewing በወለጋ ጎቡ ሰዩ ወረዳ አኖ ከተማ ጥር 25/2015 ጥቃት መድረሱን ተከትሎ በርካታ ተፈናቃዮች ወደ ደብረብርሃን ሸሽተዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     የካቲት 15 ቀን 2015 ዓ/ም…

በወለጋ ጎቡ ሰዩ ወረዳ አኖ ከተማ ጥር 25/2015 ጥቃት መድረሱን ተከትሎ በርካታ ተፈናቃዮች ወደ ደብረብርሃን ሸሽተዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 15 ቀን 2015 ዓ/ም…

በወለጋ ጎቡ ሰዩ ወረዳ አኖ ከተማ ጥር 25/2015 ጥቃት መድረሱን ተከትሎ በርካታ ተፈናቃዮች ወደ ደብረብርሃን ሸሽተዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 15 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን ጎቡ ሰዩ ወረዳ አኖ ከተማ ጥር 25/2015 ዓ.ም ጥቃት ወዲህ በርካቶች አካባቢውን ለቀው ወደ ደብረ ብርሃን ከተማ መሄዳቸው ተገልጧል፡፡ በአኖ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የተፈናቀሉ ወይም ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች አሁንም በስጋት ውስጥ እንደሚገኙ ይናገራሉ፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ በጎቡ ሰዩ ወረዳ የነበሩ ነዋሪዎች ከጥቃቱ ወዲህ አካባቢውን ለቀው መሄዳቸውን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ጠቁመዋል፡፡ የምስራቅ ወለጋ ዞን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት ወይም በአዲሱ ስያሜው “ቡሳ ጉኖፋ” ኃላፊ አቶ ዳኜ ላቺሳ በጎቡ ሰዩ 5 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ተፈናቅለው እንደነበር ተናግረዋል፡፡ አቶ ሙህዲን ኢስማኤል በጎቡ ሰዩ ወረዳ አኖ ከተማ ነዋሪ የነበሩ ሲሆን ጥር 25/2015 ዓ.ም በወረዳው ጥቃት መድረሱን ተከትሎ ወደ ደብረ ብርሀን መሸሻቸውን ተናግረዋል፡፡ በጎቡ ሰዩ የአካባቢውን ሠላም ለማስከበር የጸጥታ ሀይሎች ቢመደቡም ሰዎች በስጋት ምክንያት ወደ ሌላ ስፍራ እየሄዱ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡ በጥቃቱ ወቅት ንብታቸው መውደሙንና 2 ልጆቻውን ይዞ ወደ ደብረ ብርሀን መሄዳቸውን አመልክተዋል፡፡ ለደህንነታቸውን ስለምሰጉ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ሌላው የአኖ ከተማ ነዋሪም በከተማው ውስጥ ንብረታቸው የወደመና ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ሰብአዊ ድጋፍ እንዳልደረሳቸው ተናግረዋል፡፡ በወረዳው የሚገኙ ጸጥታ ሐይሎች ለስራ በሚንቀሳቀሱት ወቅት ድንገት በታጣቂዎች ጥቃት ሊደርስብን ይችላል በሚል ስጋት ሰዎች እንደሚሸሹም ገልጸዋል፡፡ ብዙ ቁጥር ያላቸው ነዋሪዎች ወደ አምቦና ደብረብርሀን መሄዳቸው እንዲሁም ሌሎች ደግሞ በጸጥታ ሀይሎቸ እንዳይሄዱ መመለሳቸውን አክለዋል፡፡ ከኦሮምያ ተፈናቅለዉ ባህርዳር የሚገኙ ነዋሪዎች በጎቡ ሰዩ ወረዳ አኖ ከተማ ውስጥ የሚገኘውን የሲንቄ ባንክ ባልደረባ የሆነውን ወንድማቸውን ጥር 25/2015 ዓ.ም በነበረው ጥቃት ማጣታቸውን የነገሩን ሌላው ነዋሪም ምንም ሰብአዊ ድጋፍ እንደላገኙ ተናግረዋል፡፡ በአኖ ከተማ አሁን ላይ ብዙም እንቅስቃሴ የለም ሰዎች በፍርሀት ነው እየኖሩ የሚገኙት፤ የጸጥታ ችግር ከተፈጠረ ወዲህ ሰዎች እየተጠያየቁ አይደለም፡፡ ወንድሜ ሲንቄ ባንክ ይሰራ ነበር በዕለቱ በጥይት ነው ተመቶ ህይወቱ ያለፈው፡፡ ሰብአዊ ድጋፍም በእጀባም ቢሆን እንዲመጣልን ጠይቀን ነበር እስካሁን የደረሰልን የለም ብለዋል፡፡ የጸጥታ ችግር በተደጋገመባቸው እንደ ኪረሙ ፣ ጊዳ አያና እና ጎቡ ሰዩ ወረዳን ጨምሮ ከጥቅምት ወር መጨረሻ አንስቶ 120 ሽህ ሰዎች ተፈናቅለው ይገኛሉ፡፡ በጎቡ ሰዮ አኖ ከተማ አሁን ከ5 ሺ እስከ 6 ሽህ የሚደርሱ የተፈናቀሉ ሰዎች ይገኛሉ፡፡ ሰብአዊ ደጋፍን በተመለከተም በዞኑ አስተዳደር፣ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶችም እንደ ዎርልድ ቪዥን፣ እንደ ሴቭ ዘ ችልድረን ያሉ ተቋማትና ቀይመስቀል ባደረጉልን እገዛ ድጋፍ ለማድርስ ጥረት አድረገናል ብለዋል ኃላፊው፡፡ ድጋፉ ከተፈነቃይ ቁጥር አንጻር ግን በቂ ነው ብለን አናምንም ሲሉም አክለዋል፡፡ በምስራቅ ወለጋ በተለያዩ ጊዜ በተከሰቱት የጸጥታ ችግሮች በመቶ ሽህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ሲፈናቀሉ በርካቶች ህይወታቸውን ማጣታቸው ሲዘገብ ቆይቷል፡፡ በምዕራብ ኦሮሚያ ከ7 መቶ ሺ በላይ ሰዎች ተፈናቅለው እንደሚገኙ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዩች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከዚህ በፈት ያወጣው ረፖርት ያመለክታል፡፡ አጉልዞ ጥያቄ እንዳጋራው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply