You are currently viewing በወልቂጤ ከተማ ለተከታታይ አራተኛ ቀን የስራ እንቅስቃሴ ተቋርጧል! የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የካቲት ስምንት ቀን የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች በዉሃ አቅርቦት መቋረጥ ምክን…

በወልቂጤ ከተማ ለተከታታይ አራተኛ ቀን የስራ እንቅስቃሴ ተቋርጧል! የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የካቲት ስምንት ቀን የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች በዉሃ አቅርቦት መቋረጥ ምክን…

በወልቂጤ ከተማ ለተከታታይ አራተኛ ቀን የስራ እንቅስቃሴ ተቋርጧል! የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የካቲት ስምንት ቀን የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች በዉሃ አቅርቦት መቋረጥ ምክንያት ሰላማዊ ሰልፍ ካደረጉ እና የጸጥታ አካላት በወሰዱት እርምጃ የሰዉ ህይወት ከተቀጠፈበት በኋላ ለተከታታይ አራተኛ ቀን የስራም ሆነ ሌላ እንቅስቃሴ በከተማዋ መቋረጡን ብስራት ራዲዮ ከከተማዋ ነዋሪዎች ሰምቷል። በሰልፉ ጣቢያችን ከአንድ ስማቸዉ እንዲጠቀስ ካልፈለጉ የዞኑ መንግስት ባለስልጣን እንዳረጋገጠዉ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን መዘገቡ ይታወሳል። በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በትናንትናው እለት ባወጣው መግለጫ ይህንኑ አረጋግጦ ሶስቱ ሰዎች ጭንቅላታቸዉን እና ደረታቸዉን በጥይት ተመትተዉ ሞተዋል ያለ ሲሆን ሌሎች 30 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው አስታዉቋል። ይህንን በማስመልከት የከተማዋ ነዋሪ ቅሬታዉን ለማሳየት በሚመስል ለተከታታይ አራተኛ ቀናት ከስራም ሆነ ሌላ እንቅስቃሴ በመገደብ በቤት ተቀምጧል ተብሏል። በዛሬዉ እለትም ባንኮችን ጨምሮ የመንግስት መስሪያቤቶች እና የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ከስራ ዉጪ ናቸዉ ብለዋል። አያይዘዉም የዞኑም ሆነ የከተማዋ አስተዳደር ለነዋሪዎች ጥያቄ ተገቢዉን ምላሽ እየሰጠ አለመሆኑንም ተናግረዋል። በተጨማሪም የእስካሁኑን ችግር በሚመለከት የዞኑ መንግስት ጉዳዩን የያዘበት መንገድ የሚያስተቸዉ መሆኑንም ገልጸዋል። በሌላ በኩል መንግስትን ከነዋሪው ጋር ለማጋጨት እየሰራችሁ ነዉ የተባሉ ወጣቶች እስር እየተፈጸመባቸው መሆኑንም ጣቢያችን ሰምቷል ሲል ብስራት ሬዲዮ ነው የዘገበው። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply