በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ታላቅ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ አሻራ ሚዲያ  ሰኔ 3 ቀን 2013 ዓ.ም በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የሁመራ ከተማ ሴቶች ትናንት ሰኔ 2 ቀን…

በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ታላቅ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ አሻራ ሚዲያ ሰኔ 3 ቀን 2013 ዓ.ም በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የሁመራ ከተማ ሴቶች ትናንት ሰኔ 2 ቀን…

በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ታላቅ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ አሻራ ሚዲያ ሰኔ 3 ቀን 2013 ዓ.ም በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የሁመራ ከተማ ሴቶች ትናንት ሰኔ 2 ቀን 2013 ያዘጋጁትና ያስተባበሩት ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄዷል። በዚህ በዓይነቱ ለየት ባለው የሁመራ ሴቶች የተቃውሞ ሰልፍ በከተማውና በአካባቢው የሚገኙ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሴቶች ተሳትፈዋል። በተቃውሞ ሰልፉም የውስጥ በሆነው በወልቃይት ጠገዴ አስተዳደራዊ ጉዳይ አሜሪካ እያሳየችው ያለውን ኢፍትሃዊ ጣልቃ ገብነት ተወግዞበታል፤ የአማራ ልዩ ኃይል ወልቃይት እንጅ ትግራይ ውስጥ አለመኖሩ ተገልጾበታል። አሜሪካና መሰሎቿ ለሰብአዊ መብትና ለእውነት የቆሙ ከሆነ ላለፉት 30 ዓመታት አሸባሪው ትሕነግ በወልቃይት ጠገዴ፣ጠለምት፣ራያ እንዲሁም በወለጋ፣በመተከልና በማይካድራ እና በሌሎች የፈፀመውን የዘር ማጥፋት ወንጀልን እንዲመረምሩ ተጠይቋል። ሰልፈኞቹ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በወልቃይት ጠገዴ፣ጠለምትና ራያ አማራዎች ላይ ባለፉት በርካታ ዓመታት ሆን ተብሎ የተፈፀመውን የጅምላ ፍጅት፣ እስር፣ስወራ፣ማሳደድና ማፈናቀልን መላው የኢትዮጵያ ብሎም የዓለም ህዝብ እንዲገነዘብላቸውና ከጎናቸው እንዲቆም ጠይቀዋል። ሰልፈኞቹ ማይካድራ ላይ በአማራዎች ላይ አሰቃቂ የጅምላ ፍጅት ፈፅመው ወደ ሱዳን የገቡና አሁንም ከጥፋት መንገዳቸው ያልተመለሱ የሽብር ቡድኑ አመራሮችና አባላት ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈው በህግ እንዲጠየቁ፣ከፋፋዩና ዘር አጥፊው ትሕነግም በአለም አቀፍ ፍ/ቤት ተጠያቂ እንዲሆን ጥሪ አድርገዋል። በመጨረሻም ላለፉት 30 ዓመታት የዘር ማጥፋት ወንጀል የተፈፀመበት የወልቃይት ጠገዴ፣ጠለምትና ራያ የአማራ ህዝብን ወደ ዳግም ባርነት ወይም ወደ ትሕነግና መሰሎቹ የብዝበዛና የጭቆና የአገዛዝ ቀንበር ስር እመልሳለሁ ማለት ከቶም የሚቻል አይሆንም ሲሉ በመልዕክታቸው አስተጋብተዋል ያለው አሚማ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply