You are currently viewing በወልቃይት ጠገዴ የማክሰኞ ገቢያ ከተማዋና የአካባቢው ነዋሪዎች ከተለያዩ አካባቢዎች ለጉብኝት የሚያቀኑ ወገኖችን ለመቀበል ዝግጅታቸውን አጠናቀው እየጠበቁ መሆኑ ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል…

በወልቃይት ጠገዴ የማክሰኞ ገቢያ ከተማዋና የአካባቢው ነዋሪዎች ከተለያዩ አካባቢዎች ለጉብኝት የሚያቀኑ ወገኖችን ለመቀበል ዝግጅታቸውን አጠናቀው እየጠበቁ መሆኑ ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል…

በወልቃይት ጠገዴ የማክሰኞ ገቢያ ከተማዋና የአካባቢው ነዋሪዎች ከተለያዩ አካባቢዎች ለጉብኝት የሚያቀኑ ወገኖችን ለመቀበል ዝግጅታቸውን አጠናቀው እየጠበቁ መሆኑ ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 25 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የማክሰኞ ገቢያ ከተማዋና የአካባቢው ነዋሪዎች ከተለያዩ አካባቢዎች ለጉብኝት የሚያቀኑ ወገኖችን ለመቀበል ዝግጅታቸውን አጠናቀው እየተጠባበቁ መሆኑን የወረዳው ኮሚዩኒኬሽን አስታውቋል። “አማራን እንወቅ” የሚል መርሃ ግብርን ይዘው የተነሱ ከተለያዩ የአማራ አካባቢዎች የተወጣጡ ከ600 በላይ ወገኖችን በክብር ለመቀበል ነው የተዘጋጁት። አንድነታችን የማይነጣጠልና ለጠላት የማንበገር መሆናችንን ማረጋገጫ የሆነውን ከመላው የአማራ ክልል ዞኖች የተውጣጡ ከ600 በላይ እንግዶችን ለመቀበል ስለመዘጋጀታቸው የዘገበው የኮሚዩኒኬሽን መ/ቤቱ “ወልቃይት የትግላችን መነሻ፣ የአንድነታችን ማሳያ፣ የነጻነታችን ዓርማ አማራን እንወቅ ” በሚል መርሐ ግብር ውብ የሆነውን የወልቃይት ጠገዴ ምድርንና የአካባቢውን ቱባ አማራዊ ወግ እና ባህል የሚጎበኙ ይሆናል ሲል አክሏል። ከቤታቸው ወደ ሌላኛዋ የትግል መሰረትና ቤታቸው የሚያቀኑ እንግዶችንም ለመቀበል በወልቃይት ጠገዴ ባህላዊ አለባበስ አሸብርቀውና ደምቀው ለመቀበል ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል። በጎንደር ወልቃይት ጠገዴ ዳንሻ መጋቢት 25/2014 ከተለያዩ የአማራ አካባቢዎች የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል ድግሷን አዘጋጅታ፣ የአሸናፊዎችን የሩጫ ውድድር ለማካሄድም በከፍተኛ ጉጉትና ተነሳሽነት እየጠበቀችና የሚያቀኑ እንግዶችንም እየተቀበለች ጭምር መሆኑም ተሰምቷል። ለዜናው የጠገዴ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽንን በምንጭነት ተጠቅመናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply