በወልቃይት ጠገዴ የማይካድራ ነዋሪዎች ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ የአሸባሪው ትሕነግ ወንጀለኞች በአካባቢው የፈፀሙትን የጅምላ ፍጅት በማውገዝ በሕግ እንዲጠየቁ አሳሰቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

በወልቃይት ጠገዴ የማይካድራ ነዋሪዎች ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ የአሸባሪው ትሕነግ ወንጀለኞች በአካባቢው የፈፀሙትን የጅምላ ፍጅት በማውገዝ በሕግ እንዲጠየቁ አሳሰቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

በወልቃይት ጠገዴ የማይካድራ ነዋሪዎች ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ የአሸባሪው ትሕነግ ወንጀለኞች በአካባቢው የፈፀሙትን የጅምላ ፍጅት በማውገዝ በሕግ እንዲጠየቁ አሳሰቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 27 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ከሃዲው ትሕነግ ያሰማራቸው ነፍሰ ገዳዩ ሳምረ፣ ልዩ ሀይሉና ሚሊሻው በቀናት ውስጥ ብቻ ከ700 በላይ ንፁሀን የተጨፈጨፉባት በወልቃይት ጠገዴ የማይካድራ ከተማ ነዋሪዎች ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል። ዛሬ ህዳር 27 ቀን 2013 ዓ.ም በማይካድራ ከተማ በተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ የማይካድራና የአካባቢው ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው ተሳትፈውበታል። በአይነቱ ልዩ እንደነበር በተነገረለት ሰላማዊ ሰልፍም በማይካድራ አሰቃቂ ጭፍጨፋ የፈፀመው የአሸባሪው ትሕነግ ወንጀለኞች በህግ ይጠየቁልን ስለማለታቸው የከተማው ነዋሪ ወ/ሮ ልዕልት ቸኮል ተናግረዋል። ሰልፉ እንደ ስሙ ፍፁም ሰላማዊ እና ውጤታማ እንዲሆንም የአማራ ክልል የልዩ ሀይል አባላት፣ሚሊሻዎችና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሚና ከፍተኛ እንደነበር ወ/ሮ ልዕልት ገልፀዋል። አቶ ከፍያለው አባይ የተባሉ የማይካድራ ነዋሪ በበኩላቸው በከተማው ውስጥ በአይነቱ የተለየ ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጓል ብለዋል። በሰልፉም ወልቃይት፣ጠገዴ ራያ አማራ ነው፤ አማራ ሁሌ እያለቀሰ አይኖርም፤ አማራ ሞት ይብቃው፣ የአማራ እናት ሁሌ ጥቁር አትለብስም ይብቃን፣አገራችንን እንጠብቅ፣በጀግኖቻችን መስዋዕትነት ለነጻነት ቀን በቅተናል፣ድንበራችን ተከዜ ነው፣ ወደ ሱዳን የኮበለሉ አሸባሪዎች ለህግ ይቅረቡልንና ሌሎች መልዕክቶችም መተላለፋቸውን አስታውቀዋል። ከማይካድራ ነዋሪዎች ጋር ያደረግነውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply