በወልቃይት ጠገዴ የቃብቲያ ሁመራ ነዋሪዎች ደማቅ ህዝባዊ ሰልፍ አደረጉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ.ም         አዲስ አበባ ሸዋ  በወልቃይት ጠገዴ የቃብቲያ…

በወልቃይት ጠገዴ የቃብቲያ ሁመራ ነዋሪዎች ደማቅ ህዝባዊ ሰልፍ አደረጉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በወልቃይት ጠገዴ የቃብቲያ…

በወልቃይት ጠገዴ የቃብቲያ ሁመራ ነዋሪዎች ደማቅ ህዝባዊ ሰልፍ አደረጉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በወልቃይት ጠገዴ የቃብቲያ ሁመራ ነዋሪዎች በዛሬው እለት ታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ.ም በአይነቱ የተለየና ደማቅ ህዝባዊ ሰልፍ አድርገዋል። የቃብቲያ ሁመራ ነዋሪው አቶ ሙላው አቸነፈ እንደገለፀው በተከፈለው መስዋዕትነት ከአሸባሪው ትሕነግ ግድያ፣አፈና እና ጭቆና ነጻ የወጡ የቃብቲያ ሁመራ ነዋሪዎች ዛሬ ታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ስለማድረጋቸው ተናግሯል። አቶ ሙላው ሲቀጥል ፈጣሪን ማመስገን ጀምረናል፤ እንደዚህ ብርሀን አይተን አናውቅም ነው ያለው። ከማይካድራና ከወልቃይትና ሌሎች አካባቢዎችም 3 መኪና ሙሉ አማራዎች ተገኝተው የሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊ ሆነዋል፤ ቃብቲያ ሁመራ በትሕነግ ተከልክለው በነበሩት በእነ አርቲስት ፋሲልና መሀሪ ሙዚቃዎች ደምቀዋል፤ ህዝቡም በአማራዊ ወግና ባህሉ አሸብርቆ በደስታ መሳተፉ ተገልጧል። ከህጻን እስከ አዛውንት በነቂስ ወጥተው በተሳተፉበት በዛሬው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ እኛ አማራ ነን፣ወሰናችን ተከዜ ነው፣ከትግራይ መልካም ጉርብትና እንጅ አስተዳደር አንፈልግም፣ በአማራ ክልል መስተዳደር እንፈልጋለን፣ በትሕነግ ልዩ ሀይል፣ሚሊሻና በሳምረ ላይ ተገቢ ሕጋዊ እርምጃ ይውሰድና ሌሎች በርካታ መልዕክቶች ተላልፈውበታል። ትሕነግ ምሽግ ሲቆፍርባቸው የነበሩት የወልቃይት ጠገዴና ራያ አካባቢዎች የመልሶ ልማት ያስፈልጋቸዋል የሚል መልዕክትንም አስተላልፈዋል። የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሊቀመንበር ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በስፍራው ተገኝተው ንግግር ማድረጋቸውንም ለማወቅ ተችሏል። ከቃብቲያ ሁመራ ነዋሪ ጋር የተደረገውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply