በወልቃይት ጠገዴ የወፍ አርግፍ/አዲረ መጥ ከተማ እና የአካባቢው ነዋሪዎች ከጨቋኙ እና ተስፋፊው ትሕነግ ነጻ የወጡበትን ቀን ታሳቢ በማድረግ በነቂስ አደባባይ በመውጣት ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ።…

በወልቃይት ጠገዴ የወፍ አርግፍ/አዲረ መጥ ከተማ እና የአካባቢው ነዋሪዎች ከጨቋኙ እና ተስፋፊው ትሕነግ ነጻ የወጡበትን ቀን ታሳቢ በማድረግ በነቂስ አደባባይ በመውጣት ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 4 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሽብር ተግባር ከተሰማራው ትሕነግ ነጻ የወጡ የወልቃይት፣ጠገዴ እና ራያ ነዋሪዎች በተለያዩ ጊዜያት ወደ አደባባይ በመውጣት ደስታቸውን እየገለፁ መሆኑ ይታወቃል። ከሰሞኑ የዳንሻ፣የማይካድራ፣የራያ አላማጣ፣ዋጃ፣ጥሙጋ፣ጨርጨር፣መሆኒ እና ኮረም አካባቢ ነዋሪዎች ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ የተሰማቸውን ደስታ በመግለፅ በአማራነታቸው ላይ እንደማይደራደሩ መግለጻቸው ይታወሳል። በሰላማዊ ሰልፍ ስሜታቸውን ለመግለፅና መልዕክቶችን ለማስተላለፍ እቅድ ይዘው የሰነበቱት የወፍ አርግፍ እና አካባቢው ነዋሪዎችም ዛሬ ታህሳስ 4 ቀን 2013 ዓ.ም አደባባዩን በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቃችን፣በአማራዊ ሙዚቃ፣ በአማራዊ ቱባ ወግና ባህል አደባባዩን አድምቀውት አርፍደዋል። ህዝቡ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በከፍተኛ መናበብ ያካሄደው ደማቅ ህዝባዊ ሰልፍ ፍፁም ሰላማዊ እና እኛ አማራ ነን፣ክብር ለአማራ ልዩ ሀይል፣ለፋኖ፣ለሚሊሻው እንዲሁም ክብር ለመከላከያ ሰራዊት፣ ነጻ ወጥተናል፤ ከትግራይ የሚመጣ ጥሩ ጎረቤት እንጅ አስተዳደርን አንፈልግምና የመሳሰሉ በርካታ መልዕክቶች የተላለፉበት እንደነበር ተገልጧል። ከወፍ አርግፍ ወጣት ክብረአብና ወጣት ፍቃዱን እንዲሁም ከማይካድራ አቅንታ በሰልፉ የታደመችውን ልዕልት ቸኮልን በቀጥታ የስልክ መስመራችን አግኝተን ስለሰልፉ አነጋግረናል። ሙሉ ዝግጅቱን በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply