በወልዲያ ከተማ መከላከያ በምስራቅ አማራ ፋኖ እና በህዝብ ላይ ያሳዬውን ያልተገባ አካሄድ ለማስተካከልና ሁሉንም በሚጠቅም መልኩ በንግግር ለመፍታት እየተሰራ መሆኑ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከ…

በወልዲያ ከተማ መከላከያ በምስራቅ አማራ ፋኖ እና በህዝብ ላይ ያሳዬውን ያልተገባ አካሄድ ለማስተካከልና ሁሉንም በሚጠቅም መልኩ በንግግር ለመፍታት እየተሰራ መሆኑ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 3 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ወልድያ ከተማችን ላይ ሚያዝ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ምሽት ጀምሮ ወደ መጥፎ አዝማሚያ ማምራት የጀመረው እና ሚያዝያ 2 ቀን 2014 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 10:00 በኋሏ ወደ ከፋ ችግር ሊቀየር የጀመረው ችግር ሁሉንም ሊጠቅም ወደሚችል ውይይት መድረክ ዙሯል ሲል የወልዲያ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን አስታውቋል። መረጃ ከመስጠት የዘገየነው ያልጠራ መረጃ ለሕዝባችን መስጠት ቀውስን ከመደገፍ ይቆጠራል በሚል በመሆኑ እንድትረዱን በአክብሮት እንጠይቃለንም ብሏል። ተቋሙ ሲቀጥል የሃይማኖት አባቶች ጣልቃ ገብተው በማወያየት ላይ ናቸው። ወጣቱ የሃይማኖቱ አባቶች ከሚመለከተው አካል ጋር ተወያይተው ምላሻቸውን እስከሚያሳውቁት ድረስ በትእግስት እንዲጠብቅ የሰጡትን ምክር ተቀብሎ በመጠባበቅ ላይ ነው ሲልም አክሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply