በወልዲያ ከተማ የአሸባሪውን ህወሓት ተልዕኮ ተቀብለው የጥፋት ሴራቸውን በንፁሃን ላይ ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 25 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ህዳር 3…

በወልዲያ ከተማ የአሸባሪውን ህወሓት ተልዕኮ ተቀብለው የጥፋት ሴራቸውን በንፁሃን ላይ ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 25 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 3…

በወልዲያ ከተማ የአሸባሪውን ህወሓት ተልዕኮ ተቀብለው የጥፋት ሴራቸውን በንፁሃን ላይ ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 25 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በወልዲያ ከተማ የአሸባሪውን ህወሓት ተልዕኮ ተቀብለው የጥፋት ሴራቸውን በንፁሃን ላይ ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 25 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ሰሞኑንም በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ማንነታቸውን በመቀየር በንፁሃን ላይ ሊያደርሱ የነበረውን የሽብርና የጭፍጨፋ ወንጀሎችን ሳያደርሱ በህዝቡ እና በፀጥታ ኃይሉ ትብብር በቁጥጥር ስር እየዋሉ እንደሚገኝ ኮሚሽኑ አመልክቷል። ሰሞኑን በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ አስተዳደር 25 የሽብርተኛው ህወሓትን ተልዕኮ ተቀብለው የጥፋት ሴራቸውን በንፁሃን ላይ ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የጥፋት ኃይሎች በነዋሪዎች እና በፀጥታ ኃይሉ የጋራ ጥረት በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተመልክቷል። ግለሰቦቹ በተያዙበት ወቅት የተለያዩ መታወቂያዎችን፣ከአንድ ሰው ላይ እስከ ዘጠኝ የተለያዩ የባንክ ደብተሮች በውስጣቸውም እስከ 400 ሺ ብር ድረስ ተገኝቶባቸዋል ብሏል የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን። ፖሊስም በተጠርጣሪዎች ላይ አስፈላጊውን ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝም ተመልክቷል። ዘገባው የኢቢሲ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply