በወልድያና አካባቢዋ በ15 ቀናት ውስጥ 76 ሰዎች በእብድ ውሻ ተነከሱ

በወልድያና አካባቢዋ በ15 ቀናት ውስጥ 76 ሰዎች በእብድ ውሻ ተነከሱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በወልድያ ከተማና አካባቢው በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ በእብድ ውሻ የተነከሱ 76 ሰዎች ለህክምና መምጣታቸውን የወልድያ ሆስፒታል አስታወቀ።

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ሞገስ በርየ፤ በአካባቢው የእብድ ውሻ በሽታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ መጥቷል።

በእብድ ውሻ ከተነከሱት መካከል ስድስቱ ህጻናት መሆናቸውን ገልጸው፤ ከአንድ ዓመት ህፃን እስከ 82 ዓመት አዛውንት መጎዳታቸውን ተናግረዋል።

ከአጠቃላይ ተጎጅዎች መካከል 68ቱ ከወልድያ ከተማ እንዲሁም 8ቱ ከሰሜን ወሎ ከአምስት ወረዳዎች የመጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ከተጎጅዎቹ መካከል ለ21ዱ ህሙማን በሆስፒታሉ ህክምና እንደተሰጣቸው የገለጹት ዶክተር ሞገስ፤ በሆስፒታሉ ባለው የመድሃኒት አቅርቦት እጥረት ምክንያት ቀሪዎቹ ወደ ደሴ ሆስፒታል ተልከው ህክምና እንዲያገኙ መደረጉን አመልክተዋል።

በ15 ቀናት ውስጥ 76 ሰዎች በእብድ ውሻ መነከሳቸው ችግሩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን እንደሚያመላክትም ነው የገለጹት።

ማንኛውም የእብድ ውሻ ተጠቂ ግለሰብ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ክትባትና ህክምና ማግኘት እንዳለበት ጠቁመው፤ “ይህ ካልሆነ ለሞት የሚያጋልጥ አደገኛ በሽታ ነው” ብለዋል።

በንክሻ የቆሰለውን አካልም ወዲያውኑ በሳሙናና ውሃ ማጠብና ወደ ጤና ተቋም ፈጥኖ መሄድ እንደሚያስፈልግም ነው የተናገሩት።

የወልድያ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሞላ ካሳው በበኩላቸው በከተማውና አካባቢው የእብድ ውሻ በሽታ እየተስፋፋ መምጣቱን አረጋግጠው፤ “ባለቤት አልባ ውሾች መበራከት የችግሩ ምንጭ ነው” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በወልድያና አካባቢዋ በ15 ቀናት ውስጥ 76 ሰዎች በእብድ ውሻ ተነከሱ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply