በወረባቦ እና በራያ ቆቦ ወርቄ ቀበሌ በአንበጣ መንጋ ከፍተኛ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ያደረገው ወሎ ቤተ አማራ የበጎ አድራጎት ማህበር ወደ ባቲ በማቅናት 120 ለሚሆኑ ተገጅዎች እገ…

በወረባቦ እና በራያ ቆቦ ወርቄ ቀበሌ በአንበጣ መንጋ ከፍተኛ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ያደረገው ወሎ ቤተ አማራ የበጎ አድራጎት ማህበር ወደ ባቲ በማቅናት 120 ለሚሆኑ ተገጅዎች እገዛ ማድረጉን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ወሎ ቤተ አማራ ማህበር በሰሜንና ደቡብ ወሎ እንዲሁም በኦሮሚያ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በማሳቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰባቸውን ተጎጅዎችን በጥንቃቄ በመለየት ድጋፍ ማድረጉን አስተባባሪዋ ሮዛ ሰለሞን ተናግራለች። በቅርቡ የተሰመሰረተው ወሎ ቤተ አማራ ማህበር ከሀገር ውስጥና ከውጭ ካሉ ተቆርቋሪና በጎ ፈቃደኛ ወገኖች ያሰባሰበውን ግማሽ ሚሊዮን ገንዘብ ለተጎጅዎች የሚሆኑ ድቄት፣ዘይት፣የትምህርት ቁሳቁሶችን በመግዛት ከቀናት በፊት ወደ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ራያ ቆቦ ወርቄ ቀበሌና ወረባቦ በማቅናት ለ600 ተጎጅዎች ማስረከቡ ይታወሳል። በተመሳሳይ ትናንት ህዳር 14 ቀን 2013 ዓ.ም በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ባቲ በማቅናት 120 ለሚሆኑ ወገኖች የድቄት፣የዘይትና የትምህርት ቁሳቀስ በመደገፍ አብሮነታቸውን እንደገለፁ ነው ሮዛ ሰለሞን ያስታወቀችው። ድጋፍ የተደረገላቸው የባቲ ከተማ ነዋሪዎችም በተደረገላቸው የአብሮነት ድጋፍ ደስተኛ መሆናቸውን በመግለፅ መልካም አቀባበል እንዳደረጉላቸው የተናገረችው ሮዛ የሰሜንና የደቡብ ወሎም ሆነ የኦሮሞ ብሄረሰብ የመስተዳድር አካላት ቀና ትብብራቸው አልተለየንም ብላለች፤ ምስጋናም አቅርባለች። ወሎ ቤተ አማራ ማህበር በአጠቃላይ 720 ለሚሆኑ ሰብላቸው በአንበጣ መንጋ ለተጎዳባቸው ወገኖች ድጋፍ ማድረጉንና ለቀጣይም በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ዙሪያ በርትቶ እንደሚሰራ ለማወቅ ተችሏል። ሮዛ ሰለሞን በዚህ ማህበራዊ ተሳትፎ በበጎ ፈቃደኝነት፣በንቃትና በተቆርቋሪነት የተሳተፉ ወገኖችን በሙሉ “በወጣው ይተካ” በማለት ከፍ ያለ ምስጋና አቅርባለች።

Source: Link to the Post

Leave a Reply