You are currently viewing በወረባቦ ወረዳ ገብቶ የነበረው አሸባሪው የህወሀት ቡድን በገባባቸው ቀበሌዎች የንፁሀን ዜጎችን ህይወት መቅጠፉ፣ የግለሰብ ንብረቶችንም መዝረፉና ማውደሙ አረመኔነቱን ያሳያል ተባለ። አማራ ሚዲ…

በወረባቦ ወረዳ ገብቶ የነበረው አሸባሪው የህወሀት ቡድን በገባባቸው ቀበሌዎች የንፁሀን ዜጎችን ህይወት መቅጠፉ፣ የግለሰብ ንብረቶችንም መዝረፉና ማውደሙ አረመኔነቱን ያሳያል ተባለ። አማራ ሚዲ…

በወረባቦ ወረዳ ገብቶ የነበረው አሸባሪው የህወሀት ቡድን በገባባቸው ቀበሌዎች የንፁሀን ዜጎችን ህይወት መቅጠፉ፣ የግለሰብ ንብረቶችንም መዝረፉና ማውደሙ አረመኔነቱን ያሳያል ተባለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 2 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ የ018 ቀበሌ ገላና ጎጥ ነዋሪ የሆነችውና ከአሸባሪው ህወሀት ቡድን አምልጣ የወጣችው ወ/ሮ ሀድያ ኢብራሂም እንደገለፁት ሰዎቹ ለሰው የማያዝኑ አረመኔዎች ናቸው። ” እኛ እነሱ ሲመጡ ከቤታችን ወጥተን በእርሻችን ውስጥ ነበርን፤ እፊቴ አይኔ እያያ አጎቴን አረ ደሀ ነኝ እናት የሌላቸው ልጆቼን ላሳድግ አትግደሉኝ” እያላቸው ገደሉት ብለዋል። ወ/ሮ ሀድያ ሲቀጥሉ “እኔም ሁለት ልጆችን አዝየ ሳመልጥ በሶስት ጥይት ሳቱኝ እስከ አሁን በገላና ጎጥ ብቻ አምስት ሰው ተገሎ ተገኝቷል፤ ያልተገኙ የጠፉ ሰዎችም አሉ” ብለዋል። “በየገቡበት ቦታ ሁሉ ይዘርፋሉ፤ ያገኙትን ንብረት የሚፈልጉት ከሆነ ይወስዳሉ፤ እንሰሳቶቻችንን ጨርሰውብናል፤ ያልፈለጉትን ንብረት እኛ እንዳንጠቀምበት ይሰብሩታል፤ ያቃጥሉታል” ነው ያሉት። “የእኔን ቤት ማቃጠል ጀምረውታል፤ በየቦታው ያላወደሙት ንብረት የለም፤ የእለት ጉርስ እንኳን አልተውልንም፤ ዘርፈውና ጥሬ እህላችንን መንገድ ላይ አፍስሰውታል” በማለት ተናግረዋል። ለዘገባው የወረባቦ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽንን በምንጭነት ተጠቅመናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply