በወረኢሉ ከ2 ቢሊየን በርሜል በላይ ድፍድፍ ነዳጅ በከርሰምድር ተገኘ፡፡በአማራ ክልል የአባይ ተፋሰስ አካል በሆነው ወረኢሉ በተደረገ የነዳጅ ፍለጋ ጥናት ከ2 ቢሊየን በርሜል በላይ ድፍድፍ ነ…

በወረኢሉ ከ2 ቢሊየን በርሜል በላይ ድፍድፍ ነዳጅ በከርሰምድር ተገኘ፡፡

በአማራ ክልል የአባይ ተፋሰስ አካል በሆነው ወረኢሉ በተደረገ የነዳጅ ፍለጋ ጥናት ከ2 ቢሊየን በርሜል በላይ ድፍድፍ ነዳጅ በከርሰምድር እንደሚገኝ በጥናት መታወቁን ኢ/ር ታከለ ኡማ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል።

የወረኢሉ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን በዚህ ሱሪያ ተደጋጋሚ ዘገባዎችን ሲሰራ የቆየ ሲሆን ከአመታት በፊት “ፋልከን” የተባለ የውጭ ድርጅት አካባቢው ላይ ተስፋ ሰጭ ጥናት ማድረጉን ይገልጻል።

ሀገር በቀል ድርጅትም ወረኢሉ-ወሎ ፕሮጀክት በሚል ስያሜ ከ1997-1998 ባሉት አመታት 6ወራትን የፈጀ ጥናት ማድረጉን እንዲሁም ከ3አመት በፊትም የወሎ ዩኒቨርስቲ የዘርፉ ምሁራን ናሙናዎችን ከቦታው በመውሰድና ምርምር በማድረግ በ3ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ ላይ ድፍድፍ ነዳጅ (ፔትሮሊየም) መሆኑን ማረጋገጣቸውን ይጠቅሳል።

ወረኢሉ አካባቢ ከዚህ ቀደም አንድ ኩባንያ የፍለጋ ስራ እያከናወነ የነበረ ቢሆንም፣ በአቅም እጥረት ምክንያት ስራውን ለማቋረጥ መገደዱን የማዕድን ሚኒሰትሩ ኢ/ር ታከለ ኡማ ገልጸዋል፡፡

ይህንን ጨምሮ በኢትዮጵያ አራት ተፋሰሶች ላይ የነዳጅ ፍለጋ ጥናት እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል።
አሁን መንግስት የነዳጅ ሀብቱ በአፋጣኝ ጥቅም ላይ የሚውልበትን መንገድ በማመቻቸት ላይ እንደሚገኝ ኢ/ር ታከለ ዑማ በጹሑፉቸው ገልጸዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 10 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
Website https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply