የገንዘብ ሚኒስቴር የንፅህና መጠበቂያ ምርቶች ላይ ቀረጥ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን በዚህ ሳምንት አስታውቋል። በተለይም የሴቶች የወር አበባ መጠበቂያ የሚያመርቱ ፋብሪካዎች፣ ከውጪ የሚያስገቧቸው ጥሬ እቃዎች ከቀረጥ ነፃ መሆናቸውን ታውቋል። የቀረጥ ማሻሻያው በተለይ የሴት ተማሪዎችን ህይወት ሊቀይር የሚችል መሆኑ ቢገለፅም ይህ መሻሻል እንዲመጣ ሀገር አቀፍ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የቆየው ‘ጀግኒት’ የተሰኘ ንቅናቄ ተፈፃሚነቱን ለማረጋገጥ ብዙ ስራዎች እንደሚቀሩ ያስረዳል።
Source: Link to the Post