በወቅቱ የዋጋ ክለሳ አለመደረጉ ዛሬ ላይ ለደረስንበት ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ቀውስ ምክንያት ነው የተባለ።በሃገራችን የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ ለመምጣቱ ፤የዋጋ ክለሳው መ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/POK-fyAE-dXQhJbMXYOAg0rGlI78lqVT7I9-pR_qMh3nQejbIv3znzBO5PakQaYYoEXoW-5tjathKVhBDTpQgvt0QGOiNzUcDjV1Ztc1qOZQUHTQUkIPFQVAlvFP1kn4PondN7wI-JMIoENczkDGtnQuiUc8RdHfG_T-YJ_6__w8ggFD27cjic6c9s3M5sQdIM1E-p7xCNWBnusNshu96G8e8GJakYz3EiZ0ogH6-3qNSMqr_KhM3PI4HgLXO0MranSXlSel_1awch4NuXQfdkkQU6N-QWWFqmmrjS0i3BQvg7I2tne8LrhCIHz7B-QlTCFQ67roUtRqTR9d6_tAvQ.jpg

በወቅቱ የዋጋ ክለሳ አለመደረጉ ዛሬ ላይ ለደረስንበት ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ቀውስ ምክንያት ነው የተባለ።

በሃገራችን የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ ለመምጣቱ ፤የዋጋ ክለሳው መደረግ ባለበት የጊዜ ገደብ አለመደረጉ መሆኑን የነዳጅና እና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ተወካይ አቶ አህመድ ቱሳ ተናግረዋል።

ቢያንስ በአመት 12 ጊዜ ሊከለስ የሚገባው የነዳጅ ዋጋ ፤ክለሳዉ የተደረገው 6 ጊዜ ብቻ በመሆኑ ሃገሪቱ ለተዛባ የማደያ ስርጭት እና ከፍተኛ ለሆነ የውጭ ምንዛሬ ብክነት እንድትዳረግ አድርጓታል ብለዋል፡፡

ከዚህም ባለፈ የነዳጅ ጥቁር ገበያ በመስፋፋቱ መንግስት ከዘርፋ ማግኘት የነበረበትን ገቢ በማጣቱ ለከፍተኛ ኪሳራ መዳረጉን አንስተዋል።

የመተላለፊያ ኬላዎች ላይ የሚታዩ የቁጥጥር ክፍተቶች ፤የመሠረተ ልማትና ሎጅስቲክስ ችግሮች ፤የዋጋ አስተዳደር የአሰራር ክፍተት እና ፍትሃዊ ያልሆኑ የነዳጅ ማደያ ግንባታዎች ዛሬ ሃገሪቱ ላለችበት የነዳጅ ቀውስ ተጠቃሽ ምክያቶች መሆናቸው ተወካዩ ተናግረዋል።

ይህም መንግስትን ከፍተኛ ኪሳራ ውስጥ ከመክተቱም በላይ ይደረግ የነበረውን የነዳጅ ድጎማ ለማቆም አስገድዶታል ብለዋል።
መንግስት ነዳጅን ለግል ኩባንያዎች በዱቤ ይሰጥ እንደነበር የተናገሩት አቶ አህመድ፣ አሁን ላይ ግን ቀደም ብለው በተጠቀሱ ምክኒያቶች እና ኩባንያዎቹ እዳቸውን በጊዜው እየከፈሉ ባለመሆኑ የእጅ በእጅ ሽያጭ መጀመሩን ገልፀዋል።

በአሁኑ ወቅትም ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ እዳ ያልመለሱ ድርጅቶች ጉዳይ በፍርድ ቤት እየታዬ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን

ሚያዝያ 27 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply