በወቅታዊ ሁኔታ በትግራይ ክልል ለችግር የሚዳረጉ ወገኖችን ለመደገፍ የሚውል መርሃ ግብር ይፋ ሆነ

በወቅታዊ ሁኔታ በትግራይ ክልል ለችግር የሚዳረጉ ወገኖችን ለመደገፍ የሚውል መርሃ ግብር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት በትግራይ ክልል ለችግር የሚዳረጉ ወገኖችን ለመደገፍ ጥበብ ለሃገር ክብር የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ግብረ ሃይል “የሃገር ልጅ የማር እጅ” የተሰኘ መርሃ ግብር ይፋ አደረገ፡፡

መርሃ ግብሩ መላው ኢትዮጵያውያን በትግራይ ካሉ ወገኖቹ ጎን መሆኑን በተግባር የሚያሳይበት ነው ተብሏል፡፡

በሚቀጥለው ሃሙስ ህዳር 17 ቀን 2013 ዓ.ም በሃገሪቱ ሁሉም አካባቢዎች ድጋፍ ይሰበሰባልም ተብሏል፡፡

በእለቱም የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ስፖርተኞች እና ሌሎች ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በትግራይ ላሉ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ በየተቋሙ እየዞሩ ያሰባስባሉ፡፡

በሚቀጥሉት ቀናት ይፋ በሚደረጉ በተመረጡ ቦታዎች ደግሞ ሁሉም ሰው የአቅሙን ያደርጋልም ነው የተባለው፡፡

የሚሰበሰበው ድጋፍም የገንዘብ፣ የአልባሳት፣ የምግብ እህል፣ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ጨምሮ ለወገኑ አብሮነቱን የሚያሳይበት የትኛውም ድጋፍ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

ለገቢ ማሰባሰቢያም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000354217019 የሂሳብ ቁጥር ተከፍቷል፡፡

በውጭ ላሉ ኢትዮጵያውን ደግሞ CBETETA SWIFT code አማካኝነት ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ፡፡

ጥበብ ለሃገር ክብር የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ግብረ ሃይል ባለፈው ማክሰኞ ለሃገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ የተሰኘ መርሃ ግብር ማዘጋጀቱ ይታወሳል፡፡

በአላዛር ታደለ

The post በወቅታዊ ሁኔታ በትግራይ ክልል ለችግር የሚዳረጉ ወገኖችን ለመደገፍ የሚውል መርሃ ግብር ይፋ ሆነ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply